ኢራን የተነሳላትን ማዕቀብ ፕሬዚዳንቷ አወደሱ
እሑድ፣ ጥር 8 2008
ከሰባቱ መካከል ስድስቱ የኢራን እና የዩናይትድ ስቴትስ ድርብ ዜግነት ያላቸው ናቸው። የሁለቱ አገራት በደረሱት ስምምነት መሰረት በኢራን በእስር ላይ የነበሩ አራት ሰዎች መፈታታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኑክሌር ኃይል ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የኢራን የኑክሌር መርኃ-ግብር ከተቀመጠው ውል ጋር የተስማማ መሆኑን የሚገልጥ ዘገባ ትናንት በማውጣቱ በአገሪቱ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት የጣሉትን ማዕቀብ ቅዳሜ ዕለት አንስተዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤የአውሮጳ ህብረት እና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የጣሉት ማዕቀብ በመነሳቱ ኢራን የታገደባት በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ማንቀሳቀስ ይፈቀድላታል። ምዕራባውያን ኩባንያዎች 80 ሚሊዮን ህዝብ ባላት ኢራን መሥራት የሚፈቀድላቸው ሲሆን አገሪቱ ድፍድፍ የነዳጅ ዘይትን ከአምስት አመታት በኋላ ለዓለም ገበያ ታቀርባለች። ኢራንና አምስት ሲደመር አንድ የሚባሉት ብሪታንያ፤ቻይና፤ፈረንሳይ፤ሩስያ እና ዩናይትድ ስቴትስ እንዲሁም ጀርመን በኑክሌር መርኃ-ግብር ላይ ከስምምነት ባለፈው ሐምሌ ወር የደረሱት ዓመታት ከወሰደ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በኋላ ነበር። ውሉም ኢራን የጀመረችዉን የኑክሌር መርኃ-ግብር የኑክሌር ቦንብ ለመገንባት ሳይሆን ለሲቪል አገልግሎት ብቻ እንድትጠቀም የሚፈቅድ ነበር።
እሸቴ በቀለ
ልደት አበበ