1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢራቅ የጦር ጀቶች ከሩስያ ገዛች

እሑድ፣ ሰኔ 22 2006

የእስልምና ቅዱስ ጦርነት አካኺያጅ አማፅያንን ለመዉጋት እንዲያስችል የኢራቅ መንግስት ከሩስያ የገዛቸዉ የጦር ጀቶች ኢራቅ ገቡ። እንደ ኢራቅ መንግሥት ገለፃ፤ ከሩስያ አምስት ጥቅም ላይ የዋሉ ጀቶች ኢራቅ ደርሰዋል።

https://p.dw.com/p/1CSMw
Sukhoi Su-25 Kampfflugzeug
ምስል picture-alliance/dpa

የኢራን መንግስት እንዳስታወቀው ለነዚህ የጦር ጄቶች 500 ሚሊዮን ዶላር ግድም ወጪ አድርጓል። የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር ኢራቅ ከሩስያ የገዛቻቸውን የጦር መሳሪያዎች ተጠቅማ ራሷን ለመከላከል ዝግጁ ነች ብሏል። አጠያያቂው ነገር ግን በርግጥ ኢራቅ እነዚህን የጦር ጄቶች ማብረር የሚችሉ ፓይለቶች ስለመኖሯ ነው።

የኢራቅ ወታደሮች በሱኒ የእስልምና ቅዱስ ጦርነት አካኺያጅ አማፅያን የተያዘዉን የቲክሪት ከተማን ለማስለቀቅ ትግል መጀመራቸዉ ተገልጿል። እንዲያም ሆኖ በትግሉ አሁንም የአማጵያኑ ክንድ ማየሉን የኢራቅ ጦር ኃይል ቃል አቀባይ በግልጽ ተናግረዋል። ቲክሪት፤ የቀድሞዉ የኢራቅ ፕሬዚዳንት የሳዳም ሁሴይን የትዉልድ ከተማ መሆንዋ ይታወቃል።

ISIS Kämpfer in Raqqa Syrien 14.01.2014
ምስል picture-alliance/AP Photo

እንደ ኢራቅ ጦር ሰራዊት፤ በከተማዋ የሚገኙ የሳዳም ሁሴን ደጋፊዎች አማፅያኑን ይረዳሉ። የኢራናዊያን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ኢማም ሆሚኒ፤ ኢራቅ ዉስጥ በሺዓና ሱኒ ኃይማኖት ተከታዮች መካከል የሚደረግ ጦርነት ነዉ የሚለዉን ሃሳብ ዳግም ተቃዉመዋል። እንደ አያቶላ ፤ ጦርነቱ ይልቁንም በዩኢስ አሜሪካ እንዲሁም አባር በሆኑት ምዕራባዊያን ሀገራት እና ሀገራቸዉን ነጻ ማድረግ በሚፈልጉ ኢራቃዉያን መካከል የሚደረግ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።

በኢራቅ ISIS በሚል የእንግሊዝኛ ምህጻር የታወቀው አሸባሪ የተሰኘው ሚሊሺያ ጦር፤ በኑሪ አልሚሊኪ የሚመራዉን የኢራቅ ሺዓ መንግስት በመታገል ላይ ይገኛል። የኢራቅ መንግሥት የሺዓ ሙስሊም ተከታይ ከሆነችዉ ከኢራን መንግሥትና ከዩኤስ አሜሪካ ድጋፍን ያገኛል።

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ