1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቀላል የጦር መሣሪያዎች

ረቡዕ፣ ጳጉሜን 1 2009

በግለሰቦች እጆች የሚገኙ ቀላል የጦር መሣሪያዎችን በተለያዩ መንገዶች መሰብሰብ በአፍሪቃ ሰላም ለማስፈን መፍትሄ መሆኑ ተጠቁሟል።

https://p.dw.com/p/2jSja
Pakistan immer mehr Lehrer und Schüler tragen Waffen
ምስል DW/F. Khan

ቀላል የጦር መሣሪያዎች በአፍሪቃ

 

የአፍሪቃ ኅብረት የሰላም እና የፀጥታ ኮሚሽን በአፍሪቃ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በግለሰቦች እጆች የሚገኙ ቀላል የጦር መሣሪያዎችን በተለያዩ መንገዶች መሰብሰብ መፍትሄ መሆኑን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ሰሞኑን ባካሄደው ጉባኤ ላይ ሁለት የመፍትሄ ሀሳቦች ቀርበዋል። ጉባኤውን የመሩት በኅብረቱ የቦትስዋና አምባሳደው እንዳሉት በግለሰቦች ዘንድ የሚገኙ ቀላል የጦር መሣሪያዎችን ኅብረተሰቡ በፈቃደኝነት እንዲያስረክብ ማድረግ አንዱ መንገድ ሲሆን ሌላው ደግሞ ተፋላሚ ወገኖችን አቀራርቦ ማወያየት ነው። 


ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ