1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃውያን ስደተኞች በእስራኤል

ረቡዕ፣ ኅዳር 23 2002

እስራኤል የሚገኙ መንግስት ህገ ወጥ የሚላቸው አፍሪቃውያን ስደተኞች ጉዳያቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተወሳሰበ መሄዱን አስታወቁ ።

https://p.dw.com/p/Kp9C
ምስል AP

ለዶይቼቬለ የአማርኛ ክፍል አስተያየታቸውን የሰጡት ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች እንደሚሉት በሀገሪቱ ረዥም ዓመታት የቆዩ ጥገኝነት ጠያቂዎች አንደ አዲስ አመልካች እንዲመዘገቡ እየተደረገ ሲሆን የሚሰጣቸው የስራ ፈቃድ የጊዜ ገደብም ከቀድሞው ዝቅ ብሏል ። አንዳንዶቹም ወደ ግብፅ የመባረር ስጋት ላይ ናቸው ። የእስራኤል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህገ ወጥ የተባሉትን እነዚህን ስደተኞች ወደ ግብፅ መመለስ አለመመለስ ለመወሰን ጉዳዩን እየተመለከተ ነው ።

ዜናነህ መኮንን ፣ ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ