1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃና ልማትዋ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 14 1998

ለድሆቹ አፍሪቃውያት ሀገሮች የዕዳ ስረዛ የተደረገው የአህጉሩን ልማት ለመርዳት ወይስ ምግባረ ብልሹዎቹን መንግሥታት ለመጥቀም?

https://p.dw.com/p/E0jE

ዓለም አቀፉ የገንዘብ መርሕ ድርጅት፡ አይ ኤም ኤፍ እጅግ ድሆቹ ለሆኑት የዓለም ሀገሮች፡ ብዙዎቹም በአፍሪቃ ነው የሚገኙት፡ የተሸከሙትን በሚልያርድ ዶላር የሚቆጠረውን ዕዳቸውን ሰረዘላቸው። የድርጅቱ ላዕላይ አካል ባለፈው ረቡዕ በዋሽንግተን ባሳለፈው ውሳኔው ከሀያዎቹ እጅግ ድሆች ሀገሮች መካከል አሥራ ዘጠኙ ዕዳቸውን መክፈል እንደማይኖርባቸው አመልክቶዋል። የዓለም ባንክና የአፍሪቃ የልማት ባንክም ተመሳሳይ ርምጃ እንዲወስዱ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ለድሆቹን ሀገሮች የልማት ዕድገት ዕድል ለመክፈት የተወሰደ « ታሪካዊ ውሳኔ » ይሆን ወይስ በተዛባው የልማት ፖለቲካ ፖሊሲ ላይ የሚታየው፡ ማለትም፡ አፍሪቃን በጥገኛ አድርጎ የሚያስቀራትና ምግባረ ብልሹዎቹን መንግሥታት ለመጥቀም የተወጠነ ዕቅድ ነው በሚል የአይ ኤም ኤፍ ኃላፊ ሮድሪጎ ራቶ ም አጠያይቀዋል። የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ቪም ዶርንቡሽ ስለዚሁ የዕዳ ስረዛ ውሳኔ የፃፈው አስተያየት ትርጉም እንደሚከተለው ይነበባል።