1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፋጣኝ ርዳታ ለሶማሊያ

ረቡዕ፣ ኅዳር 2 2002

የተመድ በሶማሊያ ከቤት ንብረታቸዉ ለተፈናቀሉ ወገኖች ርዳታ ለማቅረብ ያለዉ የገንዘብ መጠን እየተመናመነ መሆኑን አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/KU0s
የምግብ ርዳታ አቅራቢ ተሽከርካሪዎችምስል AP

ድርጅቱ እንደሚለዉ ቃል የገቡ ለጋሽ አገራት ባስቸኳይ እጃቸዉን ካልዘረጉ 283 ሺ የሚገመቱ ተጨማሪ ሶማሊያዉያን ስደተኞች ወደአጎራባች አገራት ለመሰደድ ይገደዳሉ። በሶማሊያ 3,6ሚሊዮን ህዝብ በአስቸኳይ የምግብ ርዳታ ኑሮዉን በመግፋት ላይ ነዉ። የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቃል አቀባይ እንደገለፁት በሶማሊያ ሰሞኑን በደረሰዉ ጎርፍ ለተፈናቀሉ ሰዎች አስፈላጊዉን ርዳታ ለማዳረስ እየተሞከረ ነዉ። የዓለም የምግብ መርሃ ግብር WFP ም ሆነ ሌሎች የመንግስታቱ ድርጅት ዘርፎች በድርቅ ለተጎዳዉ የሶማሊያ ህዝብ የምግብና ሌሎች አስፈላጊ አቅርቦቶችን በማድረግ ላይ ናቸዉ። ስራቸዉን በተገቢዉ መንገድ በማከናወን የሰዉ ህይወት ከማትረፍ ባሻገር የስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

ሸዋዬ ለገሠ/አርያም ተክሌ