1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፈርና አሳሳቢው የአፈር ማደበሪያ፤

ረቡዕ፣ ግንቦት 28 2005

ጊዜያዊ ትርፍ ፤ ዘላቂ ኪሣራ እንዳያስከትል ፤ በምርምር ፤ የተመረኮዘ ግብርና ተፈለጊ ነው። በገፍ የሚያመርቱ ትላላቅ የእርሻ ቦታዎች ያሏቸው በሰፊ ንግድ ላይ ያተኮሩ ዘመናዊ አርሶ-አደሮች ብቻ አይደሉም ይህ ጠቀሚ ምክር የሚቀርብላቸው፤ እንዲያውም

https://p.dw.com/p/18kNJ
ምስል AFP/Getty Images

ይበልጥ ምክራቸው ይበልጥ የሚፈለገው አነስተኛም ሆነ መለስተኛ የመሬት ይዞታ ላላቸው አርሶ አደሮች ነው።

ከአንድ ወር ከ 5 ቀናት በፊት በዚህ ክፍለ ጊዜ፤ «የአፍሪቃ ክፍለ ዓለም የአፈር ካርታ » በሚል ርእስ ባቀረብነው ዝግጅት ፣ የአፍሪቃ ማሳዎች፤ ያለክብካቤ፤ ከመጠን በላይ በተደጋጋሚ በመታረሣቸው፤ በአፈሩ ውስጥ የሚገኙ የተፈጥሮ ማዕድናት ስለመመናመናቸው፤ የአውሮፓው ኅብረት ያቀረበው የአፈር ካርታ እንደሚያስረዳ አውስተን እንደነበረ ይታወስ ይሆናል።

በመሃሉም፣ በዓለም ዙሪያ የዱር ዐራዊትና እንስሳት እንዲጠበቁ የሚታገለው ድርጅት World Wide Fund For Nature (WWF)(እ ጎ አ በ 1961 ዓ ም በአስዊስ አገር ሲመሠረት World Wildlife Fund በመባል ይታወቅ የነበረው ድርጅት መሆኑ ነው ፣)በተለይ የጀርመኑ ቅርንጫፍና ለጀርመን አረንጓዴ ፓርቲ የሚቀርበው ፣ ሃይንሪኽ በኧል ድርጅት፣ በኅብረት፤ ከአውሮፓው ኅብረት ጋር ተመሳሳይነት ያለው ጥናት አቅርበዋል። ርእሰ-ጉዳዩ

«የአፈር አልሚ ማዕድናት አሉታዊ ተጽእኖ በሞቃት ሃገራት ግብርና ላይ » የሚል ነው። በዚህ ርእስ ስለቀረበው ጥናት ፤ ከ WWF ያነጋገርናቸው የግብርና ባለሙያ ዶ/ር ብርጊት ቪልሄልም--ማብራሪያ አላቸዉ።

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ