አድማ በባሕርዳር
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 1 2009ማስታወቂያ
በባሕር ዳር ከቤት ያለመዉጣት አድማ መመታቱ ተሰማ። አድማዉ የተጠራዉ ቢሾፍቱ ከተማ ሊከበር በተዘጋጀዉ የኢሬቻ በዓል የሞቱ ወገኖችን ለማሰብ መሆኑ ነዉ የተመለከተዉ። የዓይን እማኞች እንደገለፁት ዛሬ የከተማዋ እንቅስቃሴ በጣም ቀዝቅዞ ነዉ የዋለዉ። ሱቆች ተዘግተዋል። አድማዉ የተጠራዉ ለአምስት ቀናት ነዉ። ዛሬ ከቀትር በኋላ ወደ ባሕርዳር በመደወል ነዋሪዎችን አነጋግረን ነበር።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ