1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሶቹ የልማት ግቦች ከቀድሞዉ ጋር ተመሳሳይ ናቸው?

ቅዳሜ፣ መስከረም 22 2008

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአረንጓዴ ልማትን በቀዳሚነት የሚያቀነቅነው የዘላቂ ልማት ግቦች የሰው ልጅ በተፈጥሮ ላይ ላሳደረው ተጽዕኖ ትኩረት የሰጠ ነው። ይህ በጣም ጥሩ ቢሆንም እጅጉን የዘገየና በቂ አይሆን ይሆን? የዶይቼ ቬለዋ ሶንያ አንጌሊካ ዴይን ትጠይቃለች።

https://p.dw.com/p/1GiEX
Symbolbild Soziale Verantwortung von Unternehmen
ምስል Fotolia/weerapat1003

[No title]


የአዲሱ ምዕተ-ዓመት የልማት ግቦች አሁን ዘላቂ የልማት ግቦች ሆነዋል። አዲሶቹን ግቦች ተዋወቋቸው። ነገር ግን ከቀደመው ጋር ተመሳሳይ አይደሉምን?
በፍጹም! የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘላቂ የልማት ግቦች እቅድ ትኩረቱን ያደረገው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ላይ ብቻ አይደለም። የአካባቢ ተፈጥሮንም ያካተተም ነዉ እንጂ!
ቁርጠኝነቱ «ዘላቂና ዘመናዊ የኃይል ምንጭን ለሁሉም» ማዳረስን ይጨምራል።
በግቦቹ ከተሞችን አረንጓዴ የማድረግ፤ የምግብ ተረፈ ምርትን በግማሽ የመቀነስ እቅድ ሰንቋል። ውቅያኖሶችን ዘላቂ በሆነ መንገድ የመጠቀም ሃሳብም ቀርቧል። ብዝሃ ህይወትም ትኩረት ተሰጥቶታል።
ለአካባቢ ተፈጥሮ የሚበጁ ነገሮችን መገንባቱ የሰው ልጅን አኗኗር ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ማካተቱ በዓለም የአካባቢ ተፈጥሮ ጉዳይ ላይ ትኩረት መሰጠቱን የሚጠቁም ምልክት ብቻ አይደለም። በትክክልም እውነተኛ ትኩረት ለዚህ ዘርፍ መስጠቱ ተገቢ ነዉ፤ የሰው ልጆች እንደማንኛውም ህይወት ያላቸው ነገሮች በተፈጥሮ ላይ ጥገኛ በመሆናቸው። የሰው ልጅ በተፈጥሮ ላይ ጥገኛ መሆን ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮን እየጎዳ ነው። ድርጊቱም መልሶ በራሳችን ደህንነት ላይ እክል መፍጠር ጀምሯል።
እናም በስተመጨረሻ ይህ በትክክል እየተሰማን ነው።
በቅሪተ-አካል የኃይል ምንጭ ላይ ጥገኛ መሆናችን ባለፉት አስርት አመታት የሰውን ልጅ የጤና ሁኔታ ወደ ኋላ እንዲጎተት እያደረገ ነዉ። እንደ ንቦች ባሉ ዝርያዎች ላይ የሚደርሰዉ ከባድ ጫናም ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ እንዳለው አሁን እውቅና ተሰጥቶታል።
እናም አዲሶቹ ዘላቂ የልማት ግቦች ከአረንጓዴ ልማት ጋር ተቆራኝተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ራሱ ቢሆን ከቀደሙት የልማት ግቦች መካከል መልሶ ወደ አዲሱ እቅድ ያካተታቸውም አሉ። ለዚህም ድህነትንና ረሐብን ማጥፋት ይጠቀሳሉ።

ቆይ ግን የምዕተ-ዓመቱ የልማት ግቦች ድህነትና ረሐብን እስካሁን አላጠፉም? ይገርማል። ግቦቹን ለማሳካት ምንም አይነት አስገዳጅ የትግበራ ጥረት አለመኖር ስኬታማ ሳያደርግ ይቀራል ብዬ አስቤ አላውቅም።
ስላቁን እንተወውና እንዲህ አይነት ዓለም አቀፍ ውሳኔዎች ስኬታማ ስለመሆናቸው ሁልጊዜም ጥርጣሬ ቢኖረኝም፤ ከምዕተ-ዓመቱ የልማት ግቦች ምን ያህሉ ስኬታማ እንደሆኑ ስረዳ ተገርሜ ነበር።
ከጎርጎሮሳዊው 2000 ጀምሮ የከፋ ድህነት ቀንሷል። በማደግ ላይ ወደሚገኙ አገሮች መድሃኒቶችን የማዳረሱ ጥረት ተጠናክሯል። በአንዳንድ የዓለም ክፍሎች የህፃናት ሞት ቀንሷል።
እንዲህ አይነት ግቦችን መያዝና ተየአካባቢ ፈጥሮን ማካተት ጥሩ እና መልካም ነው። ይህ ለተፈጥሮና አካባቢ መጠበቅ ለሚደረገዉ ጥረት የሚኖረዉን ፖለቲካዊ ፈቃደኝነት ወደ ተግባር የማሸጋገር አካል ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
መምጣቱን በተስፋ እየጠበኩ እጅግ የዘገየ እንደማይሆንም ተስፋ አደርጋለሁ።

ሶንያ አንጌሊካ ዴይን/እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሰ

Sonya Angelica Diehn Environment Team Leader Teamchefin Umwelt
ሶንያ አንጌሊካ ዴይንምስል DW/M. Müller