1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ የተመረጡት የጀርመን ፕሪዚደንት „ዮአሂም ጋዉክ”

እሑድ፣ መጋቢት 9 2004

የቀድሞው ቄስና የምሥራቅ ጀርመን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ዮአሂም ጋውክ በዛሬው ዕለት 11ኛው የፌደራል ሬፑብሊክ ጀርመን ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።

https://p.dw.com/p/14MT3
አዲሱ የጀርመን ፕሬዚደንት ዮአሂም ጋውክምስል dapd

የቀድሞው ቄስና የምሥራቅ ጀርመን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ዮአሂም ጋውክ በዛሬው ዕለት 11ኛው የፌደራል ሬፑብሊክ ጀርመን ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ። የ 72 ዓመቱ አንጋፋ ዕጩ በበርሊኑ ፓርላማ በተካሄደው የፌደራላዊ ሸንጎ ስብሰባ 991 የተውካዮች ድምጽ ሲያገኙ ለፉክክር የቀረቡት የግራ ፓርቲው ዕጩ ቤአተ ክላርስፌልድ ደግሞ በ 126 ድምጽ ተወስነው ቀርተዋል። ፌደራላዊው ሸንጎ 1240 ዓባላት ሲኖሩት ይህም የም/ቤት እንደራሴዎችንና የሕብረተሰብ ክፍላት ተጠሪዎችን የሚጠቅልል ነው። የማንኛውም ፓርቲ ዓባል ያልሆኑት ጋውክ ለዘጠኝ ዓመታት ያህል የቀድሞው ምሥራቅ ጀርመን የጸጥታ ተቋም የስታዚ ሰነድ ምርመራ ባልሥልጣን ሃላፊ ሆነው ማገልገላቸው ይታውሣል። ጋውክ ለምርጫ የቀረቡት የአገሪቱ የክርስቲያ-ሶሻል ሕብረት፣ የነጻ ዴሞክራቶች፣ የሲሻል ዴሞክራቶችና የአረንጓዴው ፓርቲ የጋራ ዕጩ ሆነው በመደገፍ ነው። ዮአሂም ጋውክ በፕሬዚደንትነት የሚተኩት ባለፈው የካቲት ወር ከሃያ ወራት ሥልጣን በኋላ ስንብት ማድረግ የተገደዱትን ክሪስቲያን ቩልፍን ነው። ክሪስቲያን ቩልፍ የዝቅተኛው ሣክሶኒያ አስተዳዳሪ በነበሩበት ጊዜ በሥልጣናቸው ተጠቃሚ ሆነዋል በሚል ጥርጣሬ አቃቤ ሕጉ በወቅቱ ምርመራ በማካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል።

አዜብ ታደሰ

መስፍን መኮንን