አዲስ አበባን የወረረው የአንበጣ መንጋ
ሐሙስ፣ ግንቦት 7 2006ማስታወቂያ
የአንበጣ መንጋ ዛሬ ከፊል አዲስ አበባን ወሯት ነበር ። በተለይ በምስራቅና ደቡብ ምሥራቅ አዲስ አበባ ዛሬ ከሰዓትበኋላ በብዛት የታየው የአንበጣ መንጋ በአንዳንድ አካባቢዎች ከመኪና መስኮቶችና ከእግረኞች ጋር እየተላተመ የትራፊክ ፍሰትን በመጠኑም ቢሆን ማስተጓጎሉ ተነግሯል ። ይሁንና አንበጣው በሌሎች አካባቢዎች እንደተለመደው በዛፎችና ሰብሎች ላይ አርፎ ከፍተኛ ጉዳት ሳይደርስ ከአካባቢው ርቋል ። ነጋሽ መሀመድ የአዲስ አበባውን ዘጋቢያችንን ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሄርን አነጋግሮታል ።
ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሄር
ነጋሽ መሀመድ