1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የኢትዮጵያ ፓርላማና ካቢኔ

እሑድ፣ መስከረም 30 2008

በ2007 አጠቃላይ ምርጫ የምክር ቤቱን መቀመጫዎች ሙሉ በሙሉ ጠቅሎ የያዘው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኢህአዴግ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ተቆጣጣሪም አስፈፃሚም ሆኖ የሚቀጥልበት ሥርዓት እንዴት ይታያል ?

https://p.dw.com/p/1Glyk
Äthiopien Parlament Hailemariam Desalegn
ምስል DW/Y. G. Egziabher

አዲሱ የኢትዮጵያ ፓርላማና ካቢኔ


5 ተኛው የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሰኞ ሥራውን የጀመረው ከ 20 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቃዋሚ ፓርቲም ሆነ የግል ተወካይ በሌለበት ነው ። በከዚህ ቀደሞቹ ምክር ቤቶች የተወሰኑም ቢሆኑ ተቃዋሚዎች ና የግል ተመራጮች መኖራቸው ቢያንስ የአንድ ፓርቲ ሃሳብ ብቻ እንዳይሰማ አድርጎ ነበር ። አሁን ግን ፓርላማው ይሄ እድል የለውም ። በ2007 አጠቃላይ ምርጫ የምክር ቤቱን መቀመጫዎች ሙሉ በሙሉ ጠቅሎ የያዘው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኢህአዴግ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ተቆጣጣሪም አስፈፃሚም ሆኖ የሚቀጥልበት አስተዳደር እንዴት ይታያል ? ወዴትስ ሊያመራ ይችላል ? በመጪው እሁድ የሚተላለፈው እንወያይ የመነጋገሪያ ነጥቦች ናቸው ።የውይይቱ ተሳታፊዎች ካነሷቸው ሃሳቦች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል ።

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ