አዲሱ የትምህርት ዘመን እና ተማሪው II
ዓርብ፣ ነሐሴ 25 2004ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ከከፍተኛ ትምህርት ፍፃሜ በኋላ ምሩቃኑ በሰለጠኑበት የስራ መስክ የመስራት እድሉ ጠባብ እንደሆነ በርካታ ወጣቶች ሲገልፁ ሰንብተዋል።
ለወጣቶቹ ስራ የሚመቻችበት አልያም በተለያዩ የስራ መስክ እንዲሰለጥኑ በት/ሚኒስቴር በኩል ስለተያዘው እቅድ አቶ ረዲ አብራርተዋል።
አንዳንድ ተማሪዎች ስራ ባያገኙ ወይንም በተማሩበት የሙያ መስክ ቀጥለው መስራት ባይፈልጉና ቀጥለው ለ2ኛ ዲግሪያቸው መማር ቢፈልጉ፤በአሁኑ ሰዓት ከበፊቱ በበለጠ ቀጥሎ የመማሩ ሁኔታ ከባድ እንደሆነ ይነገራል። ከምክንያቱ አንዱ ገንዘብ ነው። በዚህም ዙሪያ አቶ ረዲ መልስ ሰተውናል።
ተምሮ ስራ የማጣቱን ጉዳይ ለማሻሻል መፍትሄ ይሆናል ብለው የሚያስቡትን ቻሊ ለማ የተባሉ አድማጭ የላኩት አስተያየት አለ። በተማሪዎች እና በመምህራን መካከል ኩረጃን የማስፋፋት ስራ በሚስጢር እንደሚሰራ እንዲሁ አንድ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ጠቁሞናል። ሌላው አስተያየት ልጆቻችን የምእራባውያንን አጓጉል ነገሮች ሳይሆን ቴክኖሎጂዎቻቸውን እንዲቀስሙ ሁላችንም ሃላፊነት አለብን: ብለው መኮንን መላኩ የፃፉልንን አስተያየቶች በማንሳት ከአቶ ረዲ ጋ ተወያይተናል። ከሙሉ ዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
ተክሌ የኋላ