1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝደንትና ህልማቸዉ

ሰኞ፣ ጥር 25 2001

ሶማሊያ አዲስ ፕሬዝደንት አግኝታለች። ለፕሬዝደንት ቃለመሃላ የፈፀሙት ሼክ ሸሪፍ ሼክ አህመድ ከቀደም ባልደረቦቻቸዉ ይልቅ ለዘብተኛ ተብለዉ በምዕራቡ ዓለም ተቀባይነት አግኝተዋል።

https://p.dw.com/p/GloG
አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝደንት
አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝደንትምስል AP Photo/Mohamed Sheikh Nor

ቃለመሃላቸዉን ተከትሎ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃለመጠይቅ እንዳሉት ግንባር ቀደም የሚያደርጉት ተግባር ብሄራዊ እርቅ በሶማሊያ በማስፈን የአንድነት መንግስትን መመስረት ነዉ። ሼህ ሸሪፍ ሼክ አህመድ ማን ናቸዉ? ለዓመታት ስርዓተ አልበኝነት በነገሰባት ሶማሊያስ እንዳለሙት ሰላም ማስፈኑ ይሳካለቸዉ ይሆን?