1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱን ዘመን ቅበላ በዶቸ-ቬለ

አዜብ ታደሰሐሙስ፣ መስከረም 9 2000

ሙክት ከጓሮ አስረን፣ ክሽን ያለዉን የዶሮ ወጥ ሰርተን፣ የዶሮ አይን የመሰለዉን ጠላ ጠምቀን፣ ድፎዉንም ዳቦ ጋግረን ፣ ዉድ የዶቸ ቬለ ድረ-ገጽ ተከታታዮች! በሞቴ ተቃመሱልን! ባንልም በስርጭት ክፍላችን በኢትዮጽያዉያን አዲስ አመት መባቻ፣ ሰፋ ሞቅ ያለ ድግስ ደግሰን፣ ሞያችንን ባህላችን አስተዋዉቀናል።

https://p.dw.com/p/E0m9
እቴ አበባሽ እቴ አበባዪ
እቴ አበባሽ እቴ አበባዪምስል UNO

አስራ ሶስት ወር ፀሃይ የሚፈነጥቅባት ኢትዮጽያም የራስዋ የሆነ የቀን ቀመር እንዳላት፣ ዘንድሮ ሁለተኛዉን አማአት በማክበር ላይ መሆንዋን በዉጭ የምንገኝ ኢትዮጽያዉያን አስረድተናል። ጀበናዉን ጥደን ቡናዉን አንከሽክሸን ሲኒዉን ደርድረን እጣኑን አጭሰን፣ የኢትዮጽያን ባህላዊ የቡና አፈላል አሳይተናል። ኢትዮጽያ የቡና መገኛ አገር እንደሆነች ለማያዉቁ ገልጸናል። ስለ ባህላዊ መስተንግዶአችን በሰፊዉ ያድምጡ መልካም ቆይታ