1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አይሁዶችና በኢየሩሳሌም የተቀደሰዉ ተራራ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 10 2008

ኢየሩሳሌም ዉስጥ የሚገኘዉና የሰሎሞን ቤተመቅደስ ተሠርቶበት እንደነበር የሚነገርበት ስፍራ እስራኤላዉያንን ከፍልስጤማዉያን ያፋጠጠ ስፍራ ሆኗል። ቦታዉ ከሃይማኖች አኳያ ለአይሁዶችም ሆኑ ለሙስሊሞች እንዲሁም ለክርስቲያኖች የተቀደሰ ስፍራ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1GsHH
Israel Al Aqsa Moschee und Felsendom in Jerusalem
ምስል picture alliance/CPA Media

[No title]

እንዲያም ሆኖ በሃይማኖት ምክንያት እስከዛሬ ድረስ ወደዚህ ስፍራ ገብቶ መጸለይ ለአይሁዶች ሳይፈቀድ ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ከእስራኤል መንግሥት ጋር ጥሩ ግንኙነት ያላቸዉ አይሁዶች በዚህ ስፍራ ገብተዉ መጸለይ እንዲፈቀድላቸዉ እየጠየቁ ነዉ። ፍልስጤማዉያን የእስራኤል መንግሥት ፈቅዶ ያን ስፍራ ለሁለት ይከፍለዋል የሚል ስጋት አላቸዉ።

አይሁዶች ቅዱስ ሥፍራ ወይም ለእምነት የተለየ ቦታ በማለት ይጠሩታል፤ ኢየሩሳሌም ዉስጥ ቀድሞ የሰሎሞን ቤተ-መቅደስ ታንፆበት የነበረዉን ስፍራ። በአሮጌዋ ኢየሩሳሌም ዉስጥ በመሬት አቀማመጡ ከፍ ብሎ የሚታየዉ ይህ ቦታ ለአይሁዶች፤ ለክርስቲያኖችም ለሙስሊሞች የተቀደሰ ነዉ። በዓለም ዝነኛዉ አላቅሳ መስጊድ የሚገኝበትን ይህ ስፍራ ሙስሊሞች ሃርም አል ሻሪፍ ይሉታል። የእስራኤል ምክትል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲፒ ሆቶቬሊ በተደጋጋሚ በአሮጌዋ ኢየሩሳሌም የሶሎሞን ቤተ-መቅደስ በነበረበት ስፍራ በተደጋጋሚ ተገኝተዋል። እንደመንግሥት ባለስልጣንም በዚህ ስፍራ አሁን ያለዉ ሁኔታ መለወጥ ይኖርበታል፤ አይሁድ አማንያን በዚያ መጸለይ ሊፈቀድላቸዉ ይገባል ባይናቸዉ።

Russland St. Georgs Tag im Shoana Tempel
በተራራዉ ላይ የሚገኘዉ የመጮሂያ ግንብምስል picture alliance/RIA Novosti

«ስለኢየሩሳሌም ሲወራ፤ የሰሎሞን ቤተመቅደስ ከነበረበት ተራራ ዉጭ ሊሆን አይችልም። ኢየሩሳሌም የመጮሂያ ግንቡ ብቻ አይደለም። ከምንም በላይ ኢየሩሳሌም በልባችን ከዚህ ተራራ ነዉ የምትጀምረዉ።»

ሙስሊም ፍልስጤማዉያን በዚህ እንደተተነኮሱ መስሎ ይሰማቸዋል። በተቀደሰዉ ስፍራ ምክንያት ግጭትና መላምቶች ይሰማሉ፤ ኢየሩሳሌም ዉስጥ የሚገኘዉ ይህ ስፍራ በመካከለኛዉ ምሥራቅ ለተባባሰዉ ወቅታዊ ችግር አስተዋፅኦ አለዉ። ለእስራኤል አይሁዶች ከሃይማኖት አኳያ ይህ በጣም ቀላል እና ግልፅ ነዉ። ኦርቶዶክስ አይሁድ ከሚባሉት የሻዝ ፖለቲከኛ ይሳቅ ኮኸን በአሁኑ ጊዜ ወደዚያ መሄድ የተከለከለ ነዉ ይላሉ።

«የተቀደሰዉ ተራራ በጣም አስፈላጊ ነዉ። ትልቅ ትርጉም ያለዉ ስፍራ ነዉ። ሆኖም ግን አይሁዶች በአሁኑ ጊዜ ተራራዉ ላይ የሚያደርጉት ነገር የለም። ሃይማኖታዊዉ ሕግ በጥብቅ ይከለክላል።»

የ20ኛዉ ክፍለ ዘመን የአይሁድ የሃይማኖት መሪዎች ማለትም ራቢዎች ባጠቃላይ በሃይማኖት ምክንያት አይሁዶች የሰሎሞን ቤተ-መቅደስ ይገኝበት ወደነበረዉ ተራራ እንዳይገቡ ይከለክላሉ። የሃይማኖት ጉዳይ ተመራማሪ የሆኑት ቶመር ፐርሲኮ እንደሚሉት ደግሞ የእስራኤል ፖለቲከኞችም በሌላ ምክንያት አይሁዶች ወደዚያ እንዳይሄዱ እንደሚከለክሉ ያስረዳሉ።

«ይህን የማይቀበሉበት ምክንያት ከሃይማኖት ነፃ እንደሆነ አስተዳደር ከዚያ ምንም የሚያጡት ነገር ስለሌለ ነዉ። በዚያም ላይ ተራራዉ የንጉሣዉያንን ታሪክ ያካትታል። ይህ ታዲያ ራሱን የሀገር አባት ብሎ ከሚገልፅ የሶሻል ዴሞክራሲ መንግሥት ጋር እንዴት አብሮ ይሄዳል?»

በጎርጎሪዮሳዊዉ 1967ዓ,ም በተካሄደዉ ጦርነት አሮጌዋን ኢየሩሳሌም ከተቆጣጠሩ በኋላ የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ሞሼ ዳያን ይህን ስፍራ ለዮርዳኖስ አሳልፈዉ ሰጥተዋል። ከ30ዓመታት በኋላ ደግሞ ጥቂት እስራኤላዉያን ሃሳባቸዉ ሲቀይሩ፤ የአይሁድ የሃይማኖት መሪዎች ምዕራባዊ የዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻን እና የጋዛ ጎዳናዎችን ተቆጣጠሩ፤ የሰሎሞን ቤተመቅደስ የነበረበትንም ስፍራ መርገጥ ፈቀዱ። ይህ ደግሞ እንደፐርሲኮ አስተያየት ሃይማኖታዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ ርምጃ ነበር።

Israel Felsendom in Jerusalem
ባለወርቃማ ጣሪያዉ መስጊድምስል Getty Images/AFP/G. Tibbon

«የኦስሎ ስምምነት ግልፅ ነዉ። ራቢዎቹ የሰላም ስምምነቱን ራሱ በጣም ፈርተዉት ነበር። እስራኤል በዚያ ተራራ አካባቢ የነበራትን ይዞታ ታጣለች የሚል ፍርሃት ነበራቸዉ። የተወሰነዉን ክፍል መዉሰድ ፈልገዉ ነበር።»

በጎርጎሪዮሳዊዉ 2005ዓ,ም አይሁዳዉያን ሰፋሪዎች ከስፍራዉ ይነሳ መባሉ የዚህን ቡድን ታዋቂነት ከፍ አድርጎታል። የሻዝ ፖለቲከኛዉ ኮኸን የሰሎሞን ቤተመቅደስ ይገኝበት በነበረዉ ስፍራ አይሁዳዉያን እንዲፀልዩ በይፋ የሚፈቀድ ከሆነ መዘዝ አለዉ ባይ ናቸዉ። የእስራኤል ምክር ቤት ፕሬዝደንት ኤድልሽታይን ደግሞ የዚህን ስፍራ ጉዳይ እስራኤላዉያን እንዳይዘነጉት ነዉ ያሳሰቡት። የሊኩድ ፓርቲ አባላትም እንዲሁ በዚህ ስፍራ መጸለይ እንዲፈቀድ እየጠየቁ ነዉ። እንደዉም በዚህ ስፍራ አንድ የአይሁድ ቤተመቅደስ መገንባቱ ለእስራኤል ሉዓላዊነት ማረጋገጫ አድርገዉ እንደሚያዩትም ፐሪስኮ ይናገራሉ።

«ችግሩ ፖሊስ የለም፤ ኔታንያሁ ደጋግመዉ ማለት ከሚያስደስታዉ የተቀደሰዉን ተራራ በሚመለከት ያለዉ ሁኔታ አይለወጥም ከሚለዉ በቀር መንግሥት ምንም ዓይነት መመሪያ የለዉም። በተረፈ ሰዎች የፈለጉትን ነዉ የሚያደርጉት። ሄደዉ ይጸልያሉ፤ ይመለሳሉ። ይህ ደግሞ ትርምስ ነዉ።»

ቶርስተን ታይሽማን/ ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ