አውሮፓ ለመግባት የሚደረገ አደገኛ የስደት ጉዞ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 2 2001ማስታወቂያ
በዚህ ዓይነቱ ጉዞ ሜዴትራኒያን ባህር ውስጥ የሰጠሙ ፣ የባህሩ ጉዞ አልሳካ ብሏቸው በሊቢያ የሚንከራተቱ ፣ ከዚያም በባሰ ሁኔታ በሱዳንና በሊቢያ ዕስርቤቶች እንዲሁም በማልታ የስደተኞች ማጎሪያ የሚማቅቁ በርካታ ናቸው ። የተሻለ ኑሮ እና ህይወት ፍለጋ ከሞቀ ቤታቸው ፤ ከነሙሉ አካላቸው ወጥተው ለተለያዩ የጤና ችግሮች የተዳረጉም ጥቂት አይደሉም ። አንዳንዶች ደግሞ መከራውንም ችግሩንም ተቋቁመው እንደ ዕድል ማለት ይቻላል አውሮፓ ይደርሳሉ ። ከነዚህ ውስጥ ከዛሬ ሶሶት ዓመት በፊት ከአገራቸው ወጥተው ከሁለት ዓመት ስቃይና መከራ በኃላ አውሮፓ የገቡት አራት የአዲስ አበባ ልጆች ይጠቀሳሉ ። ወጣቶች ናቸው ፤ ከጓደኛቸው የሰሙትን አምነው ነበር ገንዘባቸውን ቋጥረው ከአዲስ አበባ የተንቀሳቀሱት ።
(ክፍል አንድ)
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የ.ኋላ