አውሮፓን የመታው ብርድና በረዶ ያስከተለው ችግር
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 18 2003ማስታወቂያ
እዚህ ጀርመን አንዲት ሴት የዛፍ ቅርንጫፍ ወድቆባቸው ህይወታቸው በማለፉ ፖሊስ ዝህቡ በጥንቃቄ እንዲንቀሳቀስ እየመከረ ነው ። የተከመረው በረዶ የህንፃዎችንና የመኖሪያ ቤቶችን ጣሪያዎች ደርምሷል ። በአብዛኛዎቹ አገራት የሚጥለው በረዶ እና ብርዱ ለዓመታት አጋጥሞ የማያውቅ ነው ። የአየር ፀባይ ተንባዮች እንደተናገሩት ለምሳሌ የዘንድሮው የብሪታኒያ ክረምት አገሪቱ ከ አንድ መቶ አመት ወዲህ አይታው የማታውቀው ነው ። እንደ ሌሌቹ አገራት ሁሉ ብርዱ እና በረዶው ልዩ ልዩ ዕንቅስቃሴዎችን በገታበት በብሪታኒያ በገና በዓል የተለመደው በለንደኑ Hyde park ውስጥ የሚካሄደው የማይቀረው የዋና ውድድር ውሀ በረዶ በመሆኑ ምክንያት ዘንድሮ አልተካሄደም ። ይልማ ኃሚካኤል ከበርሊን ብርዱ እና በረዶው በጀርመንና በሌሎችም የአውሮፓ አገራት ያስከተለውን ችግር ያስቃኘናል ።
ይልማ ኃሚካኤል ፣ ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ