አዉሮፕላንና ከባቢ አየር28 ታኅሣሥ 2001ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 28 2001ለዓለም የከባቢ አየር ሙቀት መጨመር ሰበብ የሆኑትን አደገኛ ጋዞች ከሚለቁ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች ባላነሰ የአየር ላይ መጓጓዣም ተጠያቂ መሆኑ ማነጋገር ከጀመረ ሰንብቷል።https://p.dw.com/p/GSzO...በፅዱ ቴክኒዎሎጂ ይተኩ...ምስል picture-alliance / dpa/dpawebማስታወቂያመፍትሄ የተባሉ ሃሳቦችም እየቀረቡ ነዉ። ነገሩ ሲታሰብ ቀላል ቢመስልም ከመቶና ሁለት መቶ በላይ ሰዎችን በአየር ላይ ለማንሳፈፍና ካሰቡበት በሰላም ለማድረስ ቴክኒዎሎጂዉ ሲፈጠር ጊዜ እንደፈጀ ሁሉ፤ እድገቱን ለማሻሻልም ጊዜ መጠየቁ ግድ ነዉ። ጅምሩና ሙከራዉ ግን ተስፋ ይሰጣል። ነገን የተሻለ ለማድረግ ጥረት ወሳኝ ነዉና።