አዉሮጳዉያን ባሪያ ፈንጋዮችና የካሳ ጥያቄ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 24 2005ማስታወቂያ
አዉሮጳዉያን ቅኝ ገዢዎችና ተስፋፋዊች አፍሪቃዉያንን እየፈነገሉ በባሪያነት በመሸጥ በመለወጣቸዉ ለዋሉት ግፍ ካሳ እንዲከፍሉ አስራ-አራት የካረቢክ አካባቢ ሐገራት የመሠረቱት ማሕበር ጠየቀ።ማሕበሩ እንደሚለዉ የአዉሮጳ ቅኝ ገዢዎችና ባሪያ ፈንጋዮች በጥንታዊ አፍሪቃዉያን ላይ የፈፀሙት ኢሠብአዊ ግፍ አሁን በካረቢክም ሆነ በተቀረዉ ዓለም ለሚገኘዉ ጥቁር ሕዝብ መደኽየትና ኋላ ቀርነት ዋና ምክንያት ነዉ።ማሕበሩ በተለይ ብሪታንያ፥ ፈረንሳይና ዳች (ወይም ኔዘርላንድን) ካሳ እንዲከፍሉ በሕግ ሊሞግታቸዉ ተዘጋጅቷል።ጠበቆች፥ አንዳድ ሙሑራንና የመብት ተሟጋቾችም የማሕበሩን አቋም እንደሚጋሩ እየተናገሩ ነዉ።የለንደንዋ ወኪላችን ሐና ደምሴ አጭር ዘገባ ልካልናለች።
ሐና ደምሴ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ