አዉሮጳና ጀርመን
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 29 2001ማስታወቂያ
ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።የዛሬዉ አዉሮጳና ጀርመን ዝግጅታችን እሁለት የሚከፈሉ ሰዎስት ጉዳዮች ይዳሰሱበታል።አለምን የመታዉ የምጣኔ ሐብት ድቀት የዕለት-ከዕለት ርዕሥ-ሥጋትም በሆነበት ዘመን-አሁን ምጣኔ-ሐብቱ ያንሰራራል-የሚል የሩቅ ተስፋ ሰሞኑን መሰማቱ አልቀረም። ተስፋዉ ግን በቅርቡ ተሰብስበዉ የነበሩት የአዉሮጳ የገንዘብ ሚንስትሮች እንዳሉት በተለይ የሥራ አጡን ቁጥር ይጨምራል የሚል ሥጋት አልተለየወም።እንደምጣኔ ሐብቱ ድቀት ሁሉ የዜጎች የግል መረጃና ሚስጥርን የመጠበቅ መብት ቢያንስ ለጀርመናዉያን አነጋጋሪ ሆኖ-ነዉ የሰነበተዉ።ሁለቱ-ርዕሶች የዝግጅታችን የመጀመሪያ ክፍል ትክረት ናቸዉ።ማንተጋፍቶት ሽለሺ አጠናቅራቸዋል።
ሁለተኛዉ ርዕሥ ወደ ለንደን ያጉዘኛል።ብሪታንያ የሚኖሩና የሚሠሩ የዉጪ ሥደተኞች፥ ሲሆን ዜግነት ይሕ ቢቀር ሕጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ እንዲሰጣቸዉ ባለፈዉ ሰኞ በሰልፍ ጠይቀዋል።ሃያ-ሺሕ የሚገመት ሥደተኛና የስደተኞች መብት ተሟጋቾች የተካፈሉበትን ሠልፍ ያደረጀዉ ለስደተኞች የሚቆረቆር ማሕበር ነዉ።የለንደንዋ ወኪላችን ሐና ደምሴ የሰልፈኛዉን ጥያቄ፥ እና የሰልፉን ሂደት ተከታትላዉ ነበር።