አወዛጋቢው የዛራትሲን መጽሐፍ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 25 2002ማስታወቂያ
ጀርመን ራሷን ለውደቅት እየዳረገች ነው” የሚል ሀሳብ የያዘው የዚህ መፀሀፍ ደራሲ የእስልምና ባሕል ጀርመን የሚኖሩ ሙስሊሞች ከህብረተሰቡ ጋር ተዋህደው እንዳይኖሩ እንቅፋት ሆኗል ሲሉ ተችተዋል ። ጀርመን ከሚኖሩ የውጭ ዜጎች በተለይ ሙስሊሞች ከህብረተሰቡ ጋር ባለመዋሀዳቸው ምክንያት ሀገሪቱን ከመጥቀም ይልቅ ሸክም እንደሆኑባት በመፀሀፋቸው ያካተቱት ሀሳብ ሙስሊሙን ህብረተሰብ በእጅጉ አስቆጥቷል ። ከጀርመንዋ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል አንስቶ የጀርመን ፖለቲከኞችም የዛራትሲንን ሀሳብ ተቃውመው አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው ።
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ
ሸዋዮ ለገስ