1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኬንያታ ድጋሚ ምርጫውን አሸንፈዋል ተብሏል

ሰኞ፣ ጥቅምት 20 2010

የኬንያ የምርጫ እና የድንበር ኮሚሽን ዛሬ እንዳስታወቀው በስልጣን ላይ ያሉት ኡሁሩ ኬንያታ 98 በመቶ ድምጽ በማግኘት በሀገሪቱ በድጋሚ የተካሄደውን ምርጫ አሸንፈዋል፡፡ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በድጋሚ እንዲካሄድ ከተወሰነው ምርጫ በኋላ በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ተቃውሞ እና ሁከት ተከስቷል፡፡

https://p.dw.com/p/2mmIe
Kenia Wahlwiederholung Uhuru Kenyatta
ምስል Reuters/S. Modola

ኬንያታ ድጋሚ ምርጫውን አሸንፈዋል ተብሏል

የኬንያ የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚሽን ሊቀመንበር ዋፉላ ቺቡካቲ ዛሬ እንደገለጹት ባለፈው ሐሙስ ጥቅምት 16 ቀን 2010 ዓ.ም በድጋሚ የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ “ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ተዓማኒ ነበር” ብለዋል፡፡ ሊቀመንበሩ ይህን ቢሉም የተቃዋሚ ፓርቲው ዕጩ የሆኑት ራይላ ኦዲንጋ ራሳቸውን ያገለሉበት ምርጫ እንዳጠያየቀ አለ፡፡ ኦዲንጋ ምርጫውን እና የወደፊት አቅጣጫቸውን አስመልከቶ ዛሬ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ እንደከዚህ ቀደሞቹ ቀናት ሁሉ ዛሬም የኦዲንጋ ደጋፊዎች በኬንያ መዲና ናይሮቢ ምርጫውን ተቃውመው ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ ከፖሊሶች ጋርም ተጋጭተዋል፡፡   

በኬንያ የአሜሪካ አምባሳደር ሮበርት ፍራንክ ጎዴክ ሀገራቸው በምርጫ ማግሥት በኬንያ የተከሰተው ሁከት በጥልቅ እንዳሳሰባት ዛሬ ገልፀዋል፡፡ ፖለቲከኞች እና መሪዎች ብጥብጡን እንዲያወግዙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የኬንያ የጸጥታ ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በሚገልጹ ሰልፈኞች ላይ የኃይል እርምጃ ከመውሰድ እንዲታቀቡ አሳስበዋል፡፡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው መግለጫ የኬንያ ፖሊስ በተቃዋሚ ደጋፊዎች እና ሰልፎች በሚካሄዱባቸው አካባቢ በነበሩ ሰዎች ላይ “ሕገ ወጥ የኃይል እርምጃ” ወስዷል ሲል ኮንኗል፡፡ ኬንያ ከምርጫ በኋላ ስላለችበት ሁኔታ ተባባሪ ዘጋቢያችንን ፍቅረማርያም መኮንን የሰጠውን ትንታኔ የድምጽ ማቀፉን በመጫን ያድምጡ፡፡

 

ፍቅረማርያም መኮንን

ተስፋለም ወልደየስ 

ሸዋዬ ለገሠ