1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አከራካሪው የግል ድርጅቶች የማህበራዊ ጡረታ ዋስትና ማሻሻያ ረቂቅ

እሑድ፣ ሰኔ 14 2007

የግል ድርጅቶች የማህበራዊ ጡረታ ዋስትና ወይም በእንግሊዝኛ አጠራሩ «በፕሮቪደንት ፈንድ » ሕግ ላይ የማሻሻያ ረቂቅ ከጥቂት ጊዜ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ነበር.

https://p.dw.com/p/1FkVa

ምክር ቤቱ ከአራት ዓመት በፊት በወጣው የፕሮቪደንት ፈንድ ሕግ ላይ ሰሞኑን በወጣው ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ባጭሩ ከተወያየበት በኋላ ጉዳዩን ለሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና ለሕግ ፍትሕ እና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል። ማሻሻያው ረቂቅ በግል ድርጅቶች ሰራተኞች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶዋል።