1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አከራካሪው የኢትዮጵያ የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ሕግ

ዓርብ፣ ጥር 1 2001

ቀደምቱ ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፤ አምነስቲያ ኢንተርናሺልና Human Rights Watch ሲቪሉን ሕብረተሰብ የሚጨቁንና የሰብዓዊ መብት ተግባራትን ለወንጀል የሚያጋልጥ ነው ሲሉ፤ ለጋሽ መንግሥታትም ትዕግሥታቸውን እያጡ በመሄድ ላይ ናቸው።

https://p.dw.com/p/GVF9
ሉድገር ሻዶምስኪ
ሉድገር ሻዶምስኪ

የኢትዮጵያ ፓርላማ ባለፈው ማክሰኞ ያጸደቀው ከመንግሥት ነጻ የሆኑ ድርጅቶች መተዳደሪያ ሕግ በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ተቃውሞ ብቻ አይደለም የቀሰቀሰው። ቀደምቱ ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፤ አምነስቲያ ኢንተርናሺልና Human Rights Watch ሲቪሉን ሕብረተሰብ የሚጨቁንና የሰብዓዊ መብት ተግባራትን ለወንጀል የሚያጋልጥ ነው ሲሉ፤ ለጋሽ መንግሥታትም ትዕግሥታቸውን እያጡ በመሄድ ላይ ናቸው።

የሕጉ ረቂቅ በተደጋጋሚ እንዲሻሻል ቢደረግም በተለይ ከአሥር ከመቶ በላይ በጀታቸውን ከውጭ የሚያገኙ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶችን የሚመለከት ሲሆን፤በሰብዓዊ መብት፣ የሴቶችና የሕጻናት መብትን በማጠናከር፤ እንዲሁም በፖለቲካ ውዝግብ አፈታት ተግባር ረገድ ከባድ መሰናክል ሊፈጥር የሚችል ነው። ሕጉ ከመጽደቁ ቀደም ሲል መንግሥት የተቃዋሚውን የዴሞክራሲና የፍትሕ ፓርቲ፤ የአንድነትን ፕሬዚደንት ወት/ብርቱካን ሚደቅሣን መልሶ ማሰሩም ከአንድ ዓመት ተኩል ገደማ በኋላ አዲስ ብሄራዊ ምርጫ በሚጠበቅባት አገር መጪውን ጊዜ ተሥፋ ሰጭ አላደረገውም። የዶቼ ቬለ ባልደረባ ሉድገር ሻዶምስኪይ በጉዳዩ ትችት-አዘል-ሃተታ ይኖረዋል።