1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አነጋጋሪው የግሪክ አዲስ ሃሳብ

ረቡዕ፣ ሰኔ 24 2007

የግሪክ መንግስት አልቀበልም ባለው አበዳሪዎች ባስቀመጧቸው ቅድመ ግዴታዎች ላይ የግሪክ ህዝብ ድምፅ እንዲሰጥ ጠይቆ ለአበዳሪዎች አዲስ ሃሳብ ይዞ መቅረቡ እያነጋገረ ነው ።

https://p.dw.com/p/1FrNo
Griechenland Ministerpräsident Alexis Tsipras
ምስል picture-alliance/ROPI

[No title]

የግሪክና የአበዳሪዎቿ ውዝግብ መፍትሄ ሳያገኝ ግሪክም ከአበዳሪዎቿ ትጠብቅ የነበረውን ገንዘብ ሳታገኝ ዕዳዋንም ሳትከፍል የተሰጣት የጊዜ ገደብ አልፏል ። የጊዜ ገደቡ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩት ትናንት የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲሲ ሲፕራስ ለአበዳሪዎች ባቀረቡት አዲስ ሃሳብ ላይ አበዳሪዎች ዛሬ ይነጋገሩበታል ። የግሪክ መንግስት አልቀበልም ባለው አበዳሪዎች ባስቀመጧቸው ቅድመ ግዴታዎች ላይ የግሪክ ህዝብ ድምፅ እንዲሰጥ ጠይቆ ለአበዳሪዎች አዲስ ሃሳብ ይዞ መቅረቡ እያነጋገረ ነው ። መፍትሄ ስላላገኘው የግሪክና የአበዳሪዎች ውዝግብ የብራሰልሱ ዘጋቢያችንን ገበያው ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ