አነጋጋሪው የጉዲፈቻ ጉዳይ
ሰኞ፣ መስከረም 11 2002ማስታወቂያ
ህፃናት ከኢትዮጵያ በማደጎ ወደ በለፀጉ ሀገራት የሚሄዱበት መንገድና ከተወሰዱ በኃላም መደረግ የሚገባው ክትትል አነጋጋሪ ከሆነ ሰነባብቷል ። አንዳንድ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች እንደሚሉት በዚህ ተግባር ውስጥ መስናና ማጭበርበር ስር ሰዷል ። በጉደፈቻ ከኢትዮጵያ የሚወጡ ህፃናት ጉዳይ የሚመለከተው የኢትዮጵያ የሴቶችና የህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ በዚህ ረገድ ከህግ ውጭ የሚከናወን ነገር የለም ሲል ያስተባብላል ። እስካሁን የጎላ ችግር አላጋጥመም የሚለው ሚኒሴቴር መስሪያ ቤቱ በጉዲፈቻ ወደ ውጭ የሚላኩ ህፃናትን መስሪያ ቤቱ እንደሚከታተል አስታውቋል ።
ታደሰ እንግዳው ፣ሒሩት መለሰ፣ ሸዋዬ ለገሠ