1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አነጋጋሪው የኢትዮጽያ የምጣኔ ሃብት ይዞታ፣

ሐሙስ፣ መስከረም 28 2002

የአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም በእንግሊዘኛዉ ምህጻሩ IMF በመባል የሚታወቀዉ ድርጅት በያዝነዉ ወር ባወጣዉ መግለጫ የኢትዮያ የምጣኔ ሃብት እድገት በ 7.2 እጅ ከመቶ ያደገ መሆኑን ቢገልጽም እድገቱ አጥጋቢ አለመሆኑን በማያያዝ አትቶአል።

https://p.dw.com/p/K2LL
6,2 ሚልዮን ያህል ሰዎች በተራቡባትና ድርቅ በተጠናወታት ኢትዮጵያ፣ 10% የኤኮኖሚ ዕድገት ይገኛል መባሉ ያስነሣው ክርክር፣ምስል AP

በሌላ በኩል በያዝነዉ ሳምንት የኢትዮጽያ ፊደሪሽን ምክር ቤት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተከፈተበት ወቅት የኢትዮጽያዉ ፕሪዝዳንት ግርማ ወልደ ጌዮርግስ የኢትዮጽያን ኢኮነሚ በ 10 እጅ ማደጉን ገልጸዋል። ይህም የአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት IMF ካለዉ እድገት በ 2 እጅ ከፍ ያለ ነዉ። የኢትዮጽያ የኢኮነሚ እድገት አለ! እየታየም ነዉ! የሚባለዉን ገለጻም ሆነ፣ የኢትዮጽያን መንግስት መግለጫ፣ በርካታ የኢኮነሚ ምሁራንን እና ሞያተኞችን እያነጋገረ ነዉ። ዝርዝሩን የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህ ያቅርብልናል።

ድልነሳ ጌታነህ/አዜብ ታደሰ/

ተክሌ የኋላ