1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተተቸው የኢሕአዴግ መግለጫ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 24 2010

በኢትዮጵያ የሚታዩ ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት ለ17 ቀናት ለስብሰባ ተቀምጦ የነበረው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባለፈው ቅዳሜ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ረዘም ያለው እና በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሰው የገዢው ፓርቲ መግለጫ እስካሁንም እያነጋገረ ይገኛል፡፡

https://p.dw.com/p/2qFTT
Äthiopien vor der Wahl EPRDF Anhänger in Addis Abeba
ምስል Reuters/Tiksa Negeri

የተተቸው የኢህአዴግ መግለጫ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫ ፓርቲው ከዚህ ቀደም ከሚያወጣቸው መግለጫዎች የተለየ ነገር ይዞ አልመጣም የሚሉ አሉ፡፡ በመግለጫው የተነሱ ጉዳዮች “ሾላ በድፍን” መሆናቸውን እና ለህዝብ በሚገባ መልኩ ተብራርተው አለመጻፋቸውን የተቹም በርካቶች ናቸው፡፡

የዋሽንግተኑ ወኪላችን ናትናኤል ወልዴ ኗሪነታቸውን በአሜሪካ ያደረጉ የፖለቲካ አራማጆች እና ታዛቢዎችን አነጋግሯል፡፡ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ዋና ዳይሬክተር ጀዋር መሐመድ፤ በኢሊኖይ ግዛት የሀርፐር ኮሌጅ ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው እና የህግ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ብርሃነመስቀል አበበ ሰኚ አስተያየታቸውን ለዶይቸ ቬለ አካፍለዋል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።   

ናትናኤል ወልዴ

ሸዋዬ ለገሠ