አነጋጋሪው የስደተኞች ጉዳይ በጀርመን
ሰኞ፣ ጥር 9 2008ማስታወቂያ
በባልካን ሃገራት በኩል ድንበር አቋርጠው ወደ ጀርመን የሚገቡ ስደተኞች በአዲሱ አመት በጎርጎሮሳዊው 2016ትም ቁጥር በቀዝቃዛው ክረምት ምክንያት ዝቅ አለ እንጂ አልቆመም ። ችግሩን ለመቋቋም የድንበር ቁጥጥርን ማጥበቅና ለስደት በቂ ምክንያት የሌላቸውን ወደ መጡበት መመለስ በመፍትሄነት የሚቀርቡ አማራጮች ሆነዋል። በተለይ በቂ የስደት ምክንያት የሌላቸውን ከሞሮኮ ከአልጀሪያና ከቱኒዝያን የሚመጡ ስደተኞችን መንግሥቶቻቸው እንዲቀበሉም ጥያቄ ቀርቧል ። ስደተኞችን በሃገራቸው በኩል የሚያሳልፉ ሌሎች የአውሮፓ ሃገራትም ድንበራቸውን እንዲቆጣጠሩ ዳግም ጥሪ ቀርቦላቸዋል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ