አነጋጋሪዉ የሶማሊያ ሰላም
ሰኞ፣ የካቲት 23 2001ማስታወቂያ
በአንፃሩ በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ እስላማዉያን ተዋጊዎች ርምጃዉን በማዋደቅ በመንግስትና ደጋፊዎቹ ላይ የጀመሩትን ዉጊያ አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ አስታዉቀዋል። አንዳንድ ወገኖች አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሶማሊያ ሰላምን ለማምጣት ይሳካላቸዋል ቢሉም የቀድሞዉን ፅንፈኛ እስላማዊ ቡድን የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅብረት ይመሩ ለነበሩት ለሼኽ ሸሪፍ ከእስላዋዉያኑ የተሰጠዉን ምላሽ በማገናዘብ የሚሆን አይመስልም ማለት ጀምረዋል።