አቶ ካኽሳይ በርኸ ተቀበሩ
ሐሙስ፣ ኅዳር 22 2009ማስታወቂያ
በቅርብ የሚያዉቋቸዉ ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት አቶ ካሕሳይ 11 ሆነዉ ወደ ደደቢት ተራራ በመጓዝ የትጥቅ ትግል ከጀመሩት የትግራይ ነፃ አዉጭ ቡድን መሥራቾች አንዱ የነበሩ ሲሆን፤ ለረዥም ዓመታት በስደት ሕይወታቸዉን ሲገፉ ቆይተዋል። በዘገባዉ ከሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ መሥራቾች አንዱ ዶክተር አረጋዊ በርሄ ፣ አቶ ካህሳይ በርሀ ከድርጅቱ እንዲባረሩ ያደረጉት የቀድሞ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን ናቸው ሲሉ ስለገለፁት፤ ከአምባሳደር ስዩም ወይም ከሕወሀት አስተያየት ለማግኘት ሞክረን ነበር ። ቤይጂንግ ስንደውል አምባሳደር ስዩም ኢትዮጵያ መሆናቸው ተነግሮን በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም በህዝብ ግንኙነታቸው በኩል ርሳቸውን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም ። የሕወሀት ሃላፊዎችንም በስልክ ማግኘት አልቻልንም ። ጥረታችን ግን ይቀጥላል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ