አቃቤ ህግ የከሰሳቸው ሙስሊሞች
ሐሙስ፣ ነሐሴ 21 2007ማስታወቂያ
የፌደራል አቃቤ ህግ በፀረ ሽብር ህግ በእነ አቡበከር መሐመድ መዝገብ 20 ሙስሊሞችን ከሷል። አብዛኛዎቹ ወጣቶች የሆኑት እነዚሁ ተከሳሾች ፣ከዚህ ቀደም በፀረ ሽብር ህግ የተከሰሱ የሙስሊሞችን መፋትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በአመፅና በብጥብጥ ለማስፈታት እንዲሁም መንግሥትን በኃይል አስወግዶ እስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት አሲረዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል ። ችሎቱ ዛሬ የተከሳሾችን የመቃወሚያ ሃሳብ በፅሁፍ ተቀብሎ ጉዳዩን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 4 2008 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ። የዛሬውን ችሎት የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር ተከታትሎታል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ