አስደንጋጩ የጀርመን አዉሮፕላን አደጋ መንስዔ
ዓርብ፣ መጋቢት 18 2007ማስታወቂያ
ይህ የ144 ተሳፋሪዎችና የ6 የበረራ ሠራተኞችን ሕይወት ያጠፋዉን የአደጋ መንስኤ የፈረንሳይና የጀርመን ፖሊሶች እንዲሁም አቃቤ ሕጉም ጭምር ባካሄዱት ምርመራ መሆኑ ተገልጿል። ይህ ምክንያት ሲሰማም በጀርመን ሕዝብ ዘንድ ዳግም ከፍተኛ ድንጋጤና ቁጣን ቀስቅሷል። ሆኖም ግን ድርጊቱ የሽብር ተግባር እንዳልሆነ የጀርመን መንግሥት የሀገር ዉስጥ አስተዳደር ሚኒስቴር በእርግጠኝነት አስታዉቆአል። የ 27 ዓመቱ ረዳት አብራሪ በመንፈስ መረበሽና ጭንቀት በሽታ ተጠምዶ እንደነበር አንዳንዶች ለብዙኃን መገናኛ ገልፀዋል። ዝርዝሩን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ልኮልናል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ