አስተያየት ስለ ጀርመንና ፖላንድ እግር ኳስ ግጥሚያ
ሐሙስ፣ ሰኔ 16 2008ማስታወቂያ
በአውሮፓ እግር ኳስ ሻምፕዮና ትናንት ጀርመን ሰሜን አየርላንድን የረታችበትን ጨዋታ አዲስ አበባ ውስጥ በርካታ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ተከታትለውታል ። በተለይም አቧሬ በሚገኘው የጀርመን ትምሕርት ቤት በዚትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ዮአሂም ሽሚትን ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ ጀርመናውያንና ኢትዮጵያውን ጨዋታውን በጋራ ሲከታተሉ ነበር ። የጀርመን ደጋፊዎች በውጤቱ ቢደሰቱም ጀርመን ከዚህም በላይ ግቦች ማስቆጠር ትችል ነበር ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ