1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሳሳቢው የማሊ ጊዚያዊ ሁኔታ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 14 2005

የማሊ መንግሥት እጅግ አደገኛ እየሆነ የመጣውን የሀገሩት ጊዚያዊ ሁኔታ ካለ ዓለም አቀፍ ርዳታ መቆጣጠር እንደማይችል ምዕራባውያን መንግሥታት ይገምታሉ። ከአል ቃይዳ ጋ ግንኙነት አላቸው የሚባሉና ሰሜናዊ ማሊን በከፊል የተቆጣጠሩት ሙሥሊም ቡድኖች ያካባቢውን ሕዝብ በማሸበር ላይ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/16VhQ
Source News Feed: EMEA Picture Service ,Germany Picture Service Fighters from the Islamic militant group the Movement for Unity and Jihad in West Africa (MUJWA) ride on a truck in the northeastern Malian city of Gao September 7, 2012. The group said on Sunday the killing of 16 Muslim preachers including eight Mauritanians and eight Malians by an army patrol in Mali was a declaration of war. MUJWA is one of the Islamic groups that has hijacked a Tuareg rebellion in northern Mali since April with the intention of imposing sharia law in the country. Picture taken September 7, 2012. REUTERS/Adama Diarra (MALI - Tags: CIVIL UNREST POLITICS CONFLICT)
የሙዣዎ ኣባልምስል Reuters

የተመድ በማሊ የምዕራብ አፍሪቃ መንግሥታት የኤኮኖሚ ማህበረሰብ ጦር ኃይል ወደ ማሊ ሊላክ የሚችልበትን መንገድ ከጥቂት ጊዜ በፊት አመቻችቶዋል። የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልም የአውሮጳ ህብረት በአክራሪ ሙሥሊም ቡድኖች አንፃር ትግል የሚያካሂደውን የማሊን ጦር ለማሰልጠን ባሰበው ተልዕኮ ውስጥ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆንዋን ገልጸዋል።
በሰሜን ማሊ በመገኙት በቲምቡክቱ፡ በጋዎ ወይም በኪዳል ከተሞች የአንሳር ዲን ወይም ሙዣዎ የተባሉት አክራሪ ቡድኖች ጥቁር ሰንደቃላማቸውን ያውልበልባሉ። እነዚህ ቡድኖች በዚሁ አካባቢ የሸሪዓን ሕግ በማስተዋወቅ ሽብራቸውን አስፋፍተዋል። ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፤ ሕፃናት በግዳጅ ለውጊያ ይመለመላሉ። ፊታቸውን ያልሸፈኑ ሴቶች የመታሰር ወይም ከዚያ የባሰ ቅጣት አስግቶዋቸዋል። ሕዝቡን በጅራፍ ይገርፋሉ፡ በድንጋይ ይወግራሉ፡ አካላቸውንን ይቆርጣሉ።
« በትልቅ ስቃይ ውስጥ ነው የምኖረው። ሰልችቶናል። ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ እንዲህ ነው የምንኖረው። እጆቻችንን ይቆርጣሉ፤ ይደፍሩናል። »
ከዚህ ሌላም፡ የእሥልምና ቅርስ የሆኑ ጥንታውያኑን መካነ መቃብሮችን ማውደማቸውን ቀጥለዋል።
« ከአንድ ሰዓት ከምሽቱ በኋላ በመንገድ አንድም ሰው አታገኝም። በጣም እንፈራለን። በቅርቡ ርዳታ እናገኛለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን። በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ነው። »
ዓለም ይህን ሁኔታ በዝምታ ለማለፍ አለመፈለጉ እየታየ ነው። የተመድ ፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ወደ ማሊ አንድ ጣልቃ የሚገባ የጦት ኃይል ሊላክ የሚችልበትን መንገድ አመቻችቶዋል። በዚህም መሠረት፡ የአፍሪቃ ህብረት እና የምዕራብ አፍሪቃ መንግሥታት የኤኮኖሚ ማህበረሰብ፡ ኤኮዋስ ሰሜናዊ ማሊን ከአክራሪዎቹ ሙሥሊሞች ቁጥጥር ነፃ ማውጣት የሚቻልበትን ዝርዝር ዕቅድ እንዲያቀርቡ የአንድ ወር ጊዜ የሰጠ ሲሆን፣ የአፍሪቃ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ኮሚሽነር ራምታን ላማምራ ውሳኔውን ደግፈውታል።
« ይህ በርግጥ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሊ ቀውስ አኳያ ወሳኝ ርምጃ መውሰዱን የሚያሳይ ነው። የማሊ መንግሥት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጣልቃ እንዲገባ በይፋ ላቀረበው ጥያቄ የተሰጠው ትክክለኛ መልስ ነው። እና አሁን የማሊን ቀውስ ለማብቃት በጋራና በቆራጥነት መስራት እንችላለን። »
ማሊ በሚገባ ያልታጠቁ ስምንት ሺህ ወታደሮች፡ በጥቂት ሺህ የሚቆጠሩ ወዶ ገቦች፡ በሁለተኛ ዓለም ጦርነት ጊዜ የነበሩ ጥቂት ታንኮች እና አንድ ተዋጊ አይሮፕላን ብቻ ነው ያሉዋት። በዚህም የተነሳ ነው አሁን ወደ ሶስት ሺህ የሚጠጉ የኤኮዋስ ወታደሮች ወደ ማሊ በመሄድ እንዲረዱ የተመድ መንገዱን ክፍት ያደረገው። በዚሁ የማሊ ተልዕኮ የሚሳተፉት አፍሪቃውያት ሀገራት ብቻ ሲሆኑ፡ በማሊ የኤኮኖሚ ጥቅም ያላት ፈረንሳይ በተዘዋዋሪ መንገድ ዘመቻውን ትደግፋለች። የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ፍራንስዋ ኦሎንድ የማሊን ዘመቻ በመሠረቱ እንደ ፀረ ሽብር ዘመቻም ነው የተመለከቱት። ባሁኑ ጊዜ ብዙ አሸባሪዎች ይህንኑ አካባቢ እንደ መሸሸጊያ ቦታ ይጠቀሙበታል ነው የሚባለው። በመሆኑም፡ ለማሊ ተልዕኮ ዩኤስ አሜሪካ በአየር ኃይሏ እና በሰው አልባው አይሮፕላንዋ አማካኝነት የስለላ መረጃ በማቅረብ እና አሸባሪዎችን በማደን፡ የአውሮጳ ህብረት አባል መንግሥታት ደግሞ ለጦሩ የሚያስፈልገውን ርዳታ በማቅረብ ይተባበራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በጀርመን መንግሥት ዘገባ መሠረት፡ የጀርመን ብሔራዊ ጦር የማሊን ጦር የሚያሰለጥኑ አንዳንድ አሰልጣኞችን ወደ ባማኮ ይልካል። ባካባቢው ካሁን ቀደም የልማት ርዳታ በመስጠት ተሞክሮ ያላት የጀርመን ምክር ቤት ሀገሩ ለማሊ የስልጣና ድጋፍ የሚሰጥበትን ውሳኔ ማጽደቅ እንዳለበት የፌዴራዊው መንግሥት የሰብዓዊ መብት ፖለቲካና የሰብዓዊ ርዳታ ተጠሪ ማርኩስ ለኒንግ አስታውቀዋል።
« በቅድሚያ ምን እንደሚያስፈልግ በጥሞና መታየት ይኖርበታል። ይህ ጥቂት ጊዜ መውሰዱ አይቀርም። ከዚያ ወደማሊ የሚላኩት ረዳቶች ምን ዓይነት ትጥቅ እና ተልዕኮ እንደሚኖራቸው መጣራት ይኖርበታል። ይህን ከማሊ መንግሥት እና ከኤኮዋስ ጋ ማቀናበር ያስፈልጋል። ከዚያ በኋላ ተልዕኮውን የጀርመን ምክር ቤትን ፈቃድ ማግኘት ይጠበቅበታል። »
ወደ ማሊ የጎረቤት ሀገራት ጦር ጣልቃ ቢገባ ቡድናቸው አፀፋ ርምጃ እንደሚወስድና አካባቢውን በጠቅላላ እንደሚያውክ የአንሳር ዲን ቃል አቀባይ ኡማር ኡልድ ሀማሃ ገልጸዋል። በወቅቱ ከምዕራብ ሰሀራ የተነሱ በመቶ የሚቆጠሩ ሙጃሂድያን ከእምነት ወንድሞቻቸው ጎን ለመሰለፍ ወደ ቲምቡክቱና ጋዎ በመገሥገሥ ላይ መሆናቸው ታውቋል።
« በፈረንሣይ፡ በዩኤስ አሜሪካ፡ በጠቅላላ በሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ኪዳን አባል ሀገራት እና በተመድ አንፃር ጭምር ለመዋጋት ዝግጁ ነን። እንደ ጥሩ ሙሥሊም እምነታችንን በትክክል መከተል አለብን። ለእምነታችንም ራሳችንን እንሰዋለን። »

In this photo taken Saturday, April 14, 2012, a Tuareg separatist rebel from the NMLA (National Movement for the Liberation of the Azawad) gestures from his vehicle, in a market in Timbuktu, Mali. West Africa's regional bloc is recommending the deployment of a regional force to Mali after Tuareg rebels declared an independent state, dubbed Azawad, following a military coup last month. Regional bloc ECOWAS said Friday, April 13 that the force would help Mali secure its territory and serve as peacekeepers. (Foto:AP/dapd)
የቱዋሬግ ዓማፅያንምስል AP
Two young fighters of the Islamist group Movement for Oneness and Jihad in West Africa (MUJAO) walk in the streets of Gao on July 17, 2012. A group of armed youths has arrived in Gao from Burkina Faso, joining hundreds of other young African recruits who have come to sign up with radical Islamists controlling the northern Mali town. AFP PHOTO / ISSOUF SANOGO (Photo credit should read ISSOUF SANOGO/AFP/GettyImages)
ሙሥሊም ተዋጊዎችምስል Getty Images
--- 2012_09_26_ecowas_truppen.psd

አሌግዛንደር ገብል/እርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ