1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሳሳቢው የሁለቱ ሱዳን መንግሥታት ፀጥታ ሁኔታ

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 25 2004

ሰሜን ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን በሚያዋስነው የጋራ ድንበር አካባቢ ውጊያው እንደቀጠለ ነው። የሱዳን ጦር ኃይላት በብሉ ናይል ግዛት በአንጻሩ የሚዋጋው ያማጽያን ቡድን ጠንካራ ሠፈር የሚገኝበትን የኩርሙክን አካባቢ ከሁለት ወራት ከባድ ውጊያ በኋላ መያዛቸውን አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/Rv3t
ምስል DW

ሥልታዊ የማፈግፈግ ርምጃ ብቻ መውሰዱን ያስታወቀው ያማጽያን ቡድን በድንበሩ አካባቢ ካለፈው ሰኔ ወር ወዲህ ውጊያ የሚያካሂደው ሦስተኛው ቡድን ሲሆን፡ የሱዳንን መንግሥት እንደሚበቀል ዝቶዋል። ቡድኑ ከብሉ ናይል ግዛት በስተምዕራብ በሚገኘው የነዳጅ ዘይት አምራች ግዛት በሆነው በደቡብ ኮርዶፋን በሱዳን መንግሥት አንጻር ከሚዋጋው የሱዳን ሕዝብ ነጻ አውጪ ንቅናቄ - ኤን ጋ የቅርብ ግንኙነት እንዳለው ይነገራል።

አርያም ተክሌ

መሥፍን መኮንን