1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሳሳቢዉ የአዲስ አበባ ቅርስ ይዞታ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 14 2006

መዲና አዲስ አበባ ፤ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርት ቤት፤ የባቡር ጣብያ ፤ የአዉሮፕላን ማረፊያ፤ የማተሚያ ቤት ሆቴሎች የስልክ ቤት፤ የመሳሰሉ ህንጻዎችን የገነባች፤ ታሪካዊ ሃዉልቶችን ያቆመች እና በኢትዮጵያ ዘመናዊነትን ከተቀበሉት የኢትዮጵያ ከተሞች በቀደምትነት ትጠቀሳለች።

https://p.dw.com/p/1A5Vb
Kaiser Menelik II. Denkmal in Addis Abeba. Kaiesr von Shoa Thema :Denkmal von Kaiser Menelik Autor /Copyright Azeb Tadesse_DW Schlagwörter. Addis Abeba Menelik II
ምስል DW

እንድያም ሆኖ 105 ኛ ዓመትን ያከበረችዉ የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ዛሪ በዘመናዊ ህንጻና በመንገድ ሥራ ግንባታ ታሪካዊ ቅርሶችዋ እየጠፉ፤ መሆናቸዉን የቅርስ ተቆርቋሪ ባለሞያዎች ይናገራሉ። አዲስ አበባ ከተማን ለማልማት በሚደረገዉ ሥራ ጥንታዊና ታሪካዊ ህንጻዎች እንዳይፈርሱ ምን እየተደረገ ነዉ? አዲስ አበባ ከተማን ለማሻሻል በሚደረገዉ ጥረት ጥንታዊ የቅርስ ይዘቶች እንዳይወድሙ ከቅርስ ጥናት ጥበቃ ባለስልጣን ጋር እየሰራን ነዉ ያሉን የኢትዮጵያ ቅርስ ባላደራ ማህበር ሊቀመንበር አቶ ጌቸዉ ታየ እንደሚሉት፤ ባለማወቅም ሆነ በማወቅ በርካታ ቅርሶች ጠፍተዋል፤ የቀሩትን መጠበቅ ይገባናል
የአዲስ አበባ ከተማ መሰረተ ልማት ለማሻሻል በሚደረገዉ ግንባታ ታሪካዊ ቅርሶች እየጠፉ መሆናቸዉን በርካቶች ይናገራሉ። ለታሪካችን ተቆርቋሪ እንደሆንን የምንታወቅ ኢትዮጵያዉያን ቅርስ ጥበቃ ላይ ብዙም ስንሰራ አይታይም የሚሉት የምህንድስና ባለሞያዉ እና የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህሩ አቶ ፋሲል ጊዮርጊስ እንደሚሉት፤
ኢትዮጵያን ፖየትሪ በሚል በፊስቡክ የግጥም ፀሃፊዎችን ያሰባሰቡትና በዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሳምሶን ደምሴ ተፈራ የሰንጋ ተራን መፍረስ አይተዉ ግጥም ጽፈዋል፤ ቢሆንም ይላሉ፤ ለልማት ሲባል በሚደረገዉ ጥረት መፍረስ የለበትም አልልም ይላሉ
እንደ ገጣሚ ሳምሶን ደምሴ ሁሉ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህሩ አቶ ፋሲል ጊዮርጊስ፤ ለልማት በሚደረገዉ ሥራ ላይ ተቃዉሞ እንደሌላቸዉ ይገልጻሉ፤ ሆኖም ግን በአዲስ አበባ ከተማ ከመፍረስ የዳኑትን ታሪካዊ ቦታዎች በጋራ መጠበቅ ይገባናል።
መሰረተ ልማትን በመዘርጋቱ ጥረት ቅርስን የመጠበቅ ሃላፊነት ሊዘነጋ አይገባም ያሉንን ባለሞያዎች ለሰጡን ቃለምልልስ እያመሰገንን፤ ሙሉዉን ቅንብር እንዲያደምጡ እንጋብዛለን።


አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ

Die Gambia Street und Churchill Avenue führen schnurgerade auf das Rathaus der äthiopischen Hauptstadt Addis Abeba. Aufnahme vom Januar 2007. Foto: Peter Smolka +++(c) dpa - Report+++
ምስል picture alliance/dpa
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ