1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አረንጓዴው ፓርቲ በኢትዮዽያ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ

ዓርብ፣ ኅዳር 17 2003

ሰሞኑን ከጀርመን ፓርቲዎች አንደኛው የሆነው አረንጓዴው ፓርቲ ኢትዮዽያን በተመለከተ ጠንከር ያለ ውሳኔ አስተላልፏል። ፓርቲው ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው በጠቅላላው ጉባዔው ላይ ነው።

https://p.dw.com/p/QJRj
አረንጓዴው ፓርቲ በኢትዮዽያ ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ
የአረንጓዴው ፓርቲ ጉባዔምስል dapd

በውሳኔው ላይ የታሰሩ የኢትዮዽያ ተቃዋሚዎች በሙሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ፓርቲው ጠይቋል። የተገደሉ ሰዎችን በተመከተም ነጻ የሆነ የፍርድ ሂደት ተመስርቶ ገዳዮች ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸው አሳስቧል። የታፈነው የኢትዮዽያ ነጻው ፕሬስም ፓርቲው ግልጽ መልዕክት በውሳኔው ላይ እስቀምጧል። አረንጓዴው ፓርቲ ጀርመንም ሆነች ሌሎች ሀገራትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለኢትዮዽያው ገዢ ፓርቲ የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል። ከበርሊን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዘገባ አለው።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ