1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሜሪካና ለአፍሪቃ የኤሌክትሪክ አቅርቦት

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 3 2009

ከሰሃራ በስተደቡብ ለሚገኙ 60 ሚሊየን ሕዝቦች ኤሎክትሪክ ለማዳረስ በቀድሞዉ የአሜሪካን ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ የተጀመረዉ መርሃግርብ እንደሚቀጥል ተገለጠ። የዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት ሰሞኑን ከሀገሪቱ ኤሌክትሪክ አቅራቢ ኩባንያዎች እና አፍሪቃዉያን ጋር በመሆን ባዘጋጀዉ መድረክ የተጀመረዉ ሥራ እንደሚቀጥል ተነግሯል።

https://p.dw.com/p/2b45c
USA Strommasten
ምስል picture alliance/blickwinkel/A. Hartl

MMT_Beri Washington (US- Africa electricity) - MP3-Stereo

30 ሺህ ሜጋ ዋት በማመንጨት ሥራዉ ላይ የሚሰማሩት የአሜሪካ፣ የካናዳ፣ የአዉሮጳ እና የእስያ ሃገራት ከፍተኛ አመራሮች ከአፍሪቃዉያን ጋር መክረዋል። ይህን አስመልክተዉ አንድ ምሁር ለዶቼ ቬለ በሰጡት ማብራሪያ ሃሳቡ ወደ ተግባር ከተለወጠ ለሰዉ ጤና፣ ለምጣኔ ሃብት እድገት፤ ለሃገራት ትስስር ለሰዎች ወደ ከተማ መሰባሰብ የጎላ ድርሻ እንደሚኖረዉ ጠቁመዋል። ዝርዝር ዘገባ መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ