1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አልጀሪያና የታገቱ የውጭ ተዋላጆች

ዓርብ፣ ጥር 10 2005

በደቡባዊው አልጀሪያ አሜናስ እተባለችው ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ጣቢያ ፣ አክራሪ እስላማውያን ታጣቂዎች፤ ይዘዋቸው የነበሩ 30 ታጋቾች ፣ 7 የውጭ አገር ተወላጆች ጭምር ፤ ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ተነገረ። ይህ የሆነው፣ የአልጀሪያ

https://p.dw.com/p/17NEl
ምስል Reuters

መንግሥት ልዩ ግብረ ኃይል ፤ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ በወሰደው እርምጃ ሳቢያ ነው። 4 ሰዎች አሁንም በአጋቾቹ ቁጥጥር ሥር ናቸው። 14 ጃፓናውያንና 8 የኖርዌይ ተወላጆች፤ የደረሱበት አልታወቀም ነው የተባለው።

የአልጀሪያ መንግሥት ፣ የታጋቾቹን ሃገራት መንግሥታት ሳያማክር በወሰደው ቅጽበታዊ  እርምጃ ቅሬታ ተፈጥሯል ።

Geiselnahme in Algerien Luftaufnahme ARCHIVBILD
ምስል Reuters

ከተገደሉት 30 ሰዎች ሌላ፤ በታጣቂ እስላማውያን  ስላተገቱት ሰዎች አኀዝና ስለተለቀቁትም ሰዎች ብዛት በየሰዓቱም ሆነ ደቂቃው፣ ከአየቅጣጫው የተለያዩ  ዜናዎች ይነገሩ እንጂ፤ አሜናስ  አጠገብ በሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ጣቢያ በትክክልና በዝርዝር ስላጋጠመው ሁኔታ የቀረበ ዘገባ የለም።  የአልጀሪያ ልዩ ግብረ ኃይል 650 ታጋቾችን አስለቅቄአለሁ ነው የሚለው። ከአነዚህ ውስጥ 70 ገደማ የሚሆኑት የውC ሃገራት ተወላጆች መሆናቸውን አስታውቋል። ከተገደሉት ቢያንስ  7 የውጫ  ሀገራት ተወላጅ ታጋቾች መካከል፣ 2 ጃፓናውያን፤ 2 የብሪታንያ ተወላጆች፤ እንዲሁም አንድ የፈረንሳይ ዜጋ እንደሚገኙበት ሮይተርስ ዜና አገልግሎት ዛሬ ረፋድ ላይ ጠቅሶ ነበር። የአልጀሪያ ዜጎች የሆኑ 8 ታጋቾች ፤ በአጋቾቹ እጅ ተገድለዋል። ከአጋቾቹም ቢያንስ 11ዱ   በአልጀሪያ ልዩ ግብረ ኃይል ነው የተገደሉት። ከእገታው ስላመለጡ በዛ ያሉ ሰዎች ዜግነት ገና የታወቀ ጉዳይ የለም። ከአልጀሪያ በጎ ዜና እንዳልተሰማ የተናገሩት የብሪታንያው ጠ/ሚንስትር ዴቪድ ኬምረን---

«የአልጀሪያ  ጠ/ሚንስትር  እንዳረጋገጡልኝ፤ የተፈጠረውን ቀውስ ለማስወገድ ማንኛውም እርምጃ ይወሰዳል። አደጋ ያንዣበበባቸው  የብሪታንያ ዜጎች ቁጥራቸው ከ 30 በታች ነው። በመጀመሪያ አኀዙ ከዚህ  የላቀ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት ነበረን።»

Algerien Geiselnahme
Algerien Geiselnahmeምስል picture alliance / dpa

ጃፓን፣  ስለሁኔታው ምንም ሳይነገራት የአልጀሪያ ጦር ኃይል  እርምጃ መውሰዱ አሳዝኗታል። ኖርዌይም ፤ የሁኔታውን አስቸጋሪነትም ሆነ ውስብስብነት ብትገነዘብም ሳይነገራት በተወሰደው እርምጃ ሳቢያ ቅር ሳትሰኝ  አልቀረችም። ከኦስሎ፣ የኖርዌይ ውጭ  ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ እንዲህ ብለዋል።

«ውጭ ጉዳይ ሚንስትራችን እንዳሉት ኖርዌይም በበኩሏ ወታደራዊ እርምጃ ከመወሰዱ በፊት ለምክክር ጥሪ ቢቀርብላት ነበረ የምትመርጠው። ያም ሆኖ ጨምረው እንዳብራሩት፤ የአልጀሪያ መንግሥት፤ በወሰደው እርምጃ ላይ ትክክል አልነበረም ብሎ አቋም ለመውሰድ ጊዜው አይፈቅድም። እርምጃው በተወሰደበት ቅጽበት፤ የነበረውን ሁኔታ አጣርቶ ማወቅ ያስፈልጋልና! መገምገም ያለበት፤ ታጋቾቹን ሁሉ የማስለቀቁ ተግባር ከተደመደመ በኋላ ነው።»

አሜናስ አቅራቢያ በሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ጣቢያ፣ አሜሪካውያን፤ ሩሜኒያውያን አንድ የኦስትሪያ ዜጋ ጭምር በአጋቾች መያዛቸውን መንግሥታቱ ያፋ አድርገዋል።

Gasfeld Algerien Geiselnahme
ምስል picture alliance / dpa

«የደም ባታሊዮን» እያለ ራሱን የሚጠራው የታጣቂ እስላማውያን ቡድን፤ አልጀሪያ ውስጥ የተጠቀሰውን እርምጃ የወሰደው፤ ፈረንሳይ ወደ ማሊ ጦር በማዝመት በአየርም በየብስም  ውስጥ የማጥቃት እርምጃ መውሰዷን በመቃወም መሆኑን አስታውቋል። በሰሐራ ምድረበዳ  ከምዕራብ እስከምሥራቅ የተለያዩ አገሮች ዜጎች የሆኑ ታጣቂዎች ተባብረው መነሳታቸውን ፤ የአፍሪቃና የምዕራባውያን መንግሥታት ሲያስገነዝቡ መቆየታቸው አይታበልም።  ከተገደሉት 11 አጋቾች መካከል፤ አልጀሪያውያኑ  2 ብቻ ናቸው ፤ ከተገደሉት መካከል አንደኛው የአጥቂው ቡድን መሪ ነበር ተብሏል። ከተገደሉት አጋቾች  መካከል፤ 3 ቱ ግብጻውያን፤ 2ቱ ቱኒሲያውያን፣ 2ቱ ሊቢያውያን፤ አንድ የማሊ፤ እንዲሁም አንድ የፈረንሳይ ዜጋ እንደነበሩ ታውቋል። ከአልጀርስ ዘግየት ብሎ በደረሰን ዜና መሠረት ከ 30 በላይ ከሚሆኑት ታጣቂዎች  18ቱ ተገድለዋል። በደቡብ አልጀሪያ የተፈጸመውን ድርጊት አስመልክተው የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ፍራንሷ ዖላንድ፣

«ሰዎችን አግቶ በቁጥጥር ሥር የማድረጉ እርምጃ የሚያሳየው፤ በማሊ ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ ለመውሰድ መወሰኑ በይበልጥ ትክክል እንደነበረ  ማለታቸው ተጠቅሷል።»

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ