1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አለመረጋጋት በጎንደር

ዓርብ፣ ሐምሌ 29 2008

በዛሬዉ ዕለት ጎንደር ከተማ ዉስጥ በፀጥታ ኃይሎች እና አደባባይ በወጡ ኗሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ አንድ ሰዉ መገደሉን የአማራ ክልል ባለሥልጣን አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/1JcMB
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

[No title]

የግጭቱን መንስኤ የተከታተሉ የአይን ምስክር ደግሞ፤ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባል የሆኑት እና በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር የሚገኙት ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ ዛሬ ጎንደር ፍርድ ቤት ይቀርባሉ የሚል መረጃ ያገኘዉ ሕዝብ ወደ ፍርድ ቤት በመሄድ የፍርዱን ሒደት ሲጠብቅ የገመተዉን በማጣቱ ሰላማዊዉ ሁኔታ ወደብጥብጥ መሻገሩን ገልጸዋል። እሳቸዉ እንደሚሉት የፀጥታ ኃይሎች ሕዝቡን ከአካባቢዉ ለመበተን በመጀመሪያ አስለቃሽ ጭስ ቀጥሎም ጥይት ተኩሰዋል። ስለሁኔታዉ የአማራ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁንን ማብራሪያ እንዲሰጡን በስልክ ጠይቀናል። በትክክል ምን ተፈጠረ ለሚለዉ ጥያቄ መልስ በመስጠት ይጀምራሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ