1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኖየር የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች መባሉ

ሰኞ፣ ነሐሴ 5 2006

የጀርመን ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድንና የባየር ሙኒክ ግብ ጠባቂ ማኑዌል ኖየር የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተባለ። ኖየርን የመረጠዉ ታዋቂዉ የጀርመን የስፖርት መጽሔት ኪከር የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዮአኺም ለቭንም የዓመቱ ምርጭ አሰልጣኝ በማለት መርጧል።

https://p.dw.com/p/1CscI
Fußball - Joachim Löw und Manuel Neuer
ምስል Getty Images

በዓለም ዋንጫ ታሪክ 16 ግብ በማስቆጠር ክብረወሰን የያዘዉ የጀርመን ብሄራዊ እግር ኳስ የፊት አጥቂ ተጫዋች እንዲሁም የባየር ሙኒክ ተጫዋች የነበረዉ ሚሮስላቭ ክሎዘ ከብሄራዊ ቡድን ተጫዋችነቱ ተሰናበተ። ቀደም ሲል የቡድኑ አምበል ፊሊፕ ላምም የጀርመኑን ብሄራዊ ቡድን ከ24ዓመታት በኋላ የዓለም ዋንጫ ባለድል በሆነች ማግስት ለብሄራዊ ቡድን እንደማይሰለፍ መግለጹ ይታወሳል።

የስፖርት ጥንቅር በእግር ኳሱ ዓለም ክለቦች አሁን ብርቱና ጠንካራ ያሉትን ተጫዋች መግዛት መቀጠላቸዉ፤ ከእንግሊዙ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አስቀድሞ ስከተካሄደዉ የኮሙኒቲ ሺልድ ዋንጫ፤ አፍሪቃ ዉስጥ የተጀመረዉን የአፍሪቃ የአትሌቲክስ ዉድድር፤የኢትዮጵያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን እንቅስቃሴና የሚያደርጋቸዉ የወዳጅነት ግጥሚያዎችንም አካቷል። ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሃይማኖት ጥሩነት

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ