1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ንግድና የአየር ጠባይ ለዉጥ

ረቡዕ፣ ጥር 12 2002

በዓለማችን የአየር ጠባይ ለዉጥ በተለይ የምግብ እህል ዋጋ መናር ሲታሰብ ድሃ አገራትን ክፉኛ ሊያጠቃቸዉ እንደሚችል ያታመናል።

https://p.dw.com/p/Lavw
ምስል Franz Badeck/PIK

ባለፉት ሁለት ዓመታት በምግብ ዋጋ ሲያሻቅብ የታየዉ እዉነታም ይህንኑ ያጠናክራል። ሁኔታዉን በቅርበት የሚከታተሉ የዘርፉ ጠቢባን ታዲያ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ የሚያደርጉት ዓለም ዓቀፉን የእርሻ ንግዱን ነዉ። የግብርና ዉጤቶች ንግድና የአየር ጠባይ ለዉጥ የተለያዩ ይምሰሉ እንጂ አንድም ሁለትም ናቸዉ። ሰለባዎቹም ያዉ መከረኞቹ ድሃዎቹ አገራትና ኅብረተሰባቸዉ ነዉ። የዶቼ ቬለዉ ማቲያስ ቡሊንገር የአየር ጠባይ ለዉጥ ከዚህ ጋ የሚያገናኘዉ ምንድነዉ ለሚለዉ ምላሽ የሚሰጥ ዘገባ አጠናቅሯል።

ሸዋዬ ለገሠ