1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኔቶ ወደ ምስራቅ አውሮፓ የተስፋፋበት አስረኛ ዓመት

ረቡዕ፣ መጋቢት 2 2001

የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት NATO ከቀዝቃዛው ጦርነት በኃላ የቀድሞ የምስራቅ አውሮፓ አገራትን በአባልነት ማስገባት ከጀመረ አስር ዓመት ሆኖታል ።

https://p.dw.com/p/HA0A
ምስል AP

እ.አ.አ መጋቢት 12 , 1999 ዓመተ ምህረት የዛሬ አስር ዓመት በኔቶ አባልነት በመታቀፍ የመጀመሪያዎቹ የቀድሞዎቹ ኮሚኒስት አገራት ፖላንድ ፣ ሀንጋሪ እና ቼክ ሪፐብሊክ ናቸው ። ከዚያን ወዲህ ኔቶ በርካታ የምስራቅ አውሮፓ ሀገራትን በማቀፍ መስፋፋቱን ቀጥሏል ። በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት በሶቭየት ህብረት ጎራ የዋርሶ የጋራ መከላከያ ኃይል አባላት የነበሩት ሶስቱ ሀገራት የዛሬ አስር ዓመት ኔቶን በመቀላቀላቸው ምን ጥቅም አገኙ ? የዶይቼቬለው ክሪስቶፍ ሀሰልባህ የዘገበውን ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።