1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ናይጀሪያ፡ ካሜሩንና የባካሲ ርክክብ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 8 2000

ናይጀሪያ በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገውን የባካሲ ልሳነ ምድር ዛሬ ለካሜሩን አስረክባለች።

https://p.dw.com/p/ExeA
የባካሲ ልሳነ ምድር
የባካሲ ልሳነ ምድርምስል AP

ርክክቡን የሚቃወሙ ወገኖች ስነ ስርዓቱን እንዳያጨናግፉ ስጋት በመፍጠሩ በትልቁ የባካሲ ልሳነ ምድር የአባና ከተማ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የሰንደቅ ዓላማ ሰቀላው ስነ ስርዓት በጸጥታ ስጋት የተነሳ ከከተማይቱ አንድ መቶ ዘጠና ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ወደካላባር ከተማ ተዛውሮዋል። በዚሁ ስነ ስርዓት የተሳተፉት የተመድ ዋና ጸሀፊ ፓን ኪ ሙን ርክክቡን ታሪካዊ ሲሉ አሞግሰዋል።