1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ናይጀሪያ እና መፃዒው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 24 1998

ኦባሳንዦ እና ለ ፫ኛ የሥልጣን ዘመን የሚወዳደሩበት ጥያናይጀሪያ ውስጥ እአአ በ 2007 ዓም ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ይካሄዳል።

https://p.dw.com/p/E0jI
በዴሞክራሲያዊ ዘዴ የተመረጡትና እአአ ከ 1999 ዓም ወዲህ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ያሉት ፕሬዚደንት ኦሉሴጉን ኦባሳንዦ በቀጣዩ ምርጫ በዕጩነት እንደማይቀርቡ በተደጋጋሚ ገልፀዋል። ይሁን እንጂ፡ ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ኦባሳንዦ ለሦስተኛ የሥልጣን ዘመን እንዲወዳደሩ አንዳንድ የሀገሪቱ ፖለቲከኞች ሀሳብ አቅርበዋል፤ ለዚህም ፕሬዚደንቱ ከሁለት የሥልጣን ዘመን በላይ እንዳይወዳደሩ የሚገድበው የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ እንዲሻሻል ጥያቄ ያቀረቡበት ድርጊት በሀገሪቱ ብዙ ክርክር አስነስቶዋል።