1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ናይጀሪያ- በአብያተ ክርስቲያን ላይ የተጣለው አደጋ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 18 2004

ቦኮ ሐራም የተባለው እስላማዊ ቡድን ናይጄሪያ ውስጥ በአብያተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት ማድረሱን አረጋግጧል። በዚህም የፈንጂ አደጋ ቢያንስ 40 ያህል ሰዎች ህይወት አልፏል።

https://p.dw.com/p/13a7d
ምስል dapd

የናይጄሪያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር አባ ሞሮ ይህን ጥቃት የሚዋጉበት ስልት እንዳወጡ ትናንት ለ አልጃዚራ ገልፀዋል።

በናይጀሪያበጎርጎሪዮሳውያንየገናበዓልዕለትበምዕመናንላይበቦኮ ሀራም እስላማዊቡድን አማካኝነት የደረሰውን ጥቃት የሀይማኖት አባቶች፣ የተለያዩ የውጭ አገር ተጠሪዎች የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀዋል። ናይጄሪያም ቦኮሐራምየተባለውእስላማዊየአማፂ ቡድንን አላማ ልታከሽፍ ማሰቧን ፤የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር -አባ ሞሮ ሲገልፁ

«የፅንፈኛውን ቡድን እንግስቃሴዎች ለመቋቋም የምንጠቀምበት ስልት የግዴታ የድርድራችን አብይ ጉዳይ ነው ብዬ አላስብም። ያንንም ስል የናይጄሪያውያንን ደህንነት ለማስጠበቅ መንግስት የመከላከያ ስልቶቹን ይቀይራል ማለት ነው።»

ዝርዝሩን ከዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ