ናይጀሪያ፡ ላይቤሪያ እና የቻርልስ ቴይለር የወደፊት ዕጣ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 19 1998ማስታወቂያ
በሲየራ ልዮን በተቋቋመው የተመድ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት የሚፈለጉትና ከ 2003 ዓም ወዲህ በግዞት ናይጀሪያ ውስጥ የሚኖሩት የቀድሞው የላይቤሪያ ፕሬዚደንት ቻርልስ ቴይለር ጉዳይና የወደፊቱ ዕጣ ፈንታቸው በወቅቱ ናይጀሪያና ላይቤሪያን እንዳነታረከ ይገኛል። ቴይለር ከ 1991 እስከ 2002 ዓም ድረስ በተካሄደው የርስበርስ ጦርነት ወቅት በፈፀሙት የጦር እና የስብዕና ወንጀል ነው ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ክስ የመሠረተባቸው።