1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኒዠር የሕዝብ ብዛትና ምጣኔ

ዓርብ፣ የካቲት 25 2008

የኒዠር የሕዝብ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ነዉ። ከሐምሳ ዓመት በፊት የበረሐማይቱ አፍሪቃዊት ሐገር ህዝብ ቁጥር 3.5 ሚሊዮን ነበ። አሁን ግን ወደ ሐያ ሚሊዮን ደርሷል።አንዳድ ዘገቦች እንደጠቆሙት በዓለም ላይ በሕዝብ ቁጥር መናር ኒጀርን የሚስተካከል ሐገር የለም።

https://p.dw.com/p/1I6vi
Niger Bevölkerungswachstum Frau mit Kindern
ምስል Getty Images/AFP/O. Omirin

የሕዝብ ቁጥሩ አለቅጥ ማደግ ለአፍሪቃዊቱ ሐገር ጊዜ ጠብቆ እንደሚፈነዳ ቦምብ አደገኛ ቀዉስ ሊያስከትል ይችላል ባዮችም አሉ። ኒያሚ ነዉ።ኒዠር ርዕሠ-ከተማ አንድ የመንግት የጤና ማዕከል።ሕፃኑ የክትባት መርፌዉ አሳምሞት ያለቅሳል።ሌላኛዉ ክፍል ከናቱ ጋር የተቀመጠዉ የዘጠኝ ወሯ ሐሊማቱ ግን እንደ ትንሹ ሕፃን የክትባት መርፌ አያሰጋትም።ምክንያቱም የዚያን ቀን እናትዋን አጅባ እንጂ-ለክትባት አይደለም የመጣችዉና። እናት መሪየማ ሶሌይ ወደ ክሊኒኩ የመጣችዉ የወሊድ መከላከያ ክሊኒኩ የመጣችዉ ለሌላ ጉዳይ ነዉ።

«የመጣሁት የወሊድ መቆጣጠሪያ ኪኒን ለመዉሰድ ነዉ።ባለፈዉ ጊዜ ለሰወስት ወር ተስጥቶች ነበር።እሱ ሥላለቀብኝ ነዉ ሌላ ለመዉሰድ የመጣሁት።» ለኒዠሮች ሴቶች ብዙም ያልተለመደ ነዉ።የ35 ዓመቷ መሪየማ ሶሌይ ግን እንደ ጥሩ መፍትሔ ታየዋለች።ባለቤቷም ይደግፋታል። «ከባለቤቴ ጋር ተጋግረንበታል።መዉሰድ የጀመርኩትም ሐሳቡን ሥለተቀበለዉ ነዉ።እንዲያዉም እሱ ነዉ ሐሳቡን ያመጣዉ።»

Heft Verhütungsmethode
ምስል DW/K. Gänsler

ባልና-ሚስት ሁለት ልጆች አሏቸዉ።ለሕክምና፤ለቀለብ፤ ለልብስ፤ እና ልጆቹ ከፍ ሲሉ ደግሞ ለትምሕርት ቤት ወጪ የሚሆን ገንዘብ መቆጠብ አለባቸዉ።ተጨማሪ ልጅ ቢመጣ ጣጣዉ ከባድ ነዉ።«ዘመናይ አስተሳሰብ» ይሉታል ኢሳካ ማጋ ሐሚዶ።ኒያሚ የሚገኘዉ የአብዱ ሞዉሙኒ ዩኒቨርስቲ የሶሲዮሎጂ መምሕር ናቸዉ። የሥነ-ተዋልዶ ባለሙያም።

«በቅርቡ በተደገ ጥናት መሠረት የኒዠር ሕዝብ በዓመት ባማካይ 3.9 ከመቶ ያድጋል።ይሕ ማለት እያንዳንዷ ሴት በአማካይ ወደ ስምንት ልጅ አላት አላት ማለት ነዉ።የዓለም ክብረ-ወሰን ማለት ነዉ።» ኒዤር ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚንቻረረዉን ሕዝቧን ለለማኖር በቂ ሥራ፤ተመጣጣኝ ምጣኔ ሐብት፤ የጤና አገልግሎት ተቋማት፤ ትምሕርት ቤቶችና መኖሪያ ቤቶች ሊኖሯት ይገባል።አንዱም የላትም።የሕዝቡን ቁጥር ከፍላጎቱ ጋር ማጣጣም በቅርቡ የሚመረጠዉ የወደፊቱ የሐገሪቱ ፕሬዝደንት የዉሎ-አምሽቶ ሐሳብ ሊሆንም ይገባም።በምረጡኝ ዘመቻዎች ግን አሳሳቢዉን ጉዳዩ ጉዳይ የጣፈዉ የለም። የሥነ-ተዋልዶዉ ባለሙያ ግን ከማሳሰብም ከባድ ነዉ ባይ ናቸዉ።

«ኒዠር ከዓለም የመጨረሻዋ ደሐ ሐገር ናት።ከዚሕ አኳያ ሲታይ የሕዝቡ ቁጥር ማደግ ከባድ ነዉ። የምጣኔ ሐብቱ ዕድገት መካከለኛ ነዉ። መፍትሔ ፍለጋዉን በጣም የሚያወሳስበዉ ይሕ እዉነት ነዉ።»
ችግሩ ኒያሚ አዉራ ጎዳናዎች ላይ አፍጥቶ ይታያል። በርካታ ወጣቶች የጉልበት ሥራ ለማግኘት ሲራኮቱ ማየት እንግዳ አይደለም። ከሐገሪቱ ሕዝብ ሰማንያ በመቶዉ የሚኖርበት አካባቢ ከልማት ጋር አይተዋወቅም። «አኒማስ ሱቱራ» የተሰኘዉ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሐላፊ ማሃሱዉ ማሐማን እንደሚሉት ማሕበረ-ባሕላዊ-ምጣኔ ሐብታዊ ተጋምዶዉን ይወቅሳሉ።

«ማሕበረሰቡ ሥለሚጠብቅ ልጅ መዉለድ እንፈልጋለን።በኛ ማሕበረሰብ አንድ ሰዉ ማንነት የሚለካዉ ባሉት ልጆች ብዛት ነዉ።ከዚሕም በተጨማሪ ልጆች በእርሻዉ መስክም ሆነ ትናንሽ ቁሳቁሶችን በመሸጥ ወላጆቻቸዉን ይረዳሉ።»
አብዛኛዉ ኒዠሪያዊ የልጆቹን ቁጥርና አቅሙን ማጣጣም እንደሚችሉ አያዉቅም።የወሊድ መቆጣጠሪያ ምክር፤መድሐኒት የሚያገኘዉም በጣም ትንሽ ነዉ።ማሐሶዉ ማሐማን የሐይማኖት መሪዎችንም ተጠያቂ ያደረጋሉ።

«የሐይማኖት አባቶች የቤተሠብ-ምጣኔን ምዕራባዉያን የሐገሪቱን ዕድገት ለማገድ የሚያደርጉት ሙከራ አካል ነዉ ብለዉ ሥለሚያምኑ አይፈቅዱም። ሥለዚሕ በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ዉይይት ያስፈልጋል። የሕፃናት እና የእናቶች ጤናም መጠበቅ አለበት።» የመሪየም ሶሌይ ሐሳብ ይሕ ነዉ። አሁን ሴት ልጇን ሐሊማቶን በማሳደጉ ላይ ታተኩራለች። ከሁለት፤ ሰወስት ዓመት በኋላ ግን ሁለተኛ ልጅ መድገም ትፈልጋለች። ግን «አላሕ ያቃል» ትላለች። «በአላሕ ፍቃድ ነዉ-የሚሆነዉ። ለሰዎች የሚያደርገዉን እሱ ያዉቃል።»

Junge Menschen im Niger
ምስል DW/K. Gänsler

ካትሪን ጌንስለር / ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ